Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-20 06:15:00
#HawassaUniversity

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ አምጥታችሁ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከየካቲት 20 እስከ 26/2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ተቋሙ ገልጿል።

የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ የካቲት 27 እና 28/2015 ዓ.ም በዋናው ግቢ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣

➧ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው፣

➧ጉርድ ፎቶግራፍ (4)

➧ የሌሊት አልባሳት

➧ የስፖርት ትጥቅ

የመልሶ ቅበላ አመልካች ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የካቲት 29 እና 30/2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@minster_of_education
2.3K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 06:14:47
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከ635 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 10 ተማሪዎች የላፕቶፕ ሽልማት ሰጥቷል።

ተሻሚዎቹ ስምንቱ ከየይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆኑ ሁለቱ ከደሴ ከተማ ትምህርት ቤት መሆናቸው ተገልጿል።

ለሽልማቱ ዩኒቨርሲቲው ከ8 መቶ 50 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጓል።

በተመሳሳይ ከ600 እስከ 634 ውጤት ላስመዘገቡ 19 ተማሪዎች የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቦርድ እና የደሴ ከተማ አስተዳደር በጋራ ለእያንዳንዳቸው ተማሪዎች የ6 ሺህ ብር ሽልማት ሰጥተዋል።

የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ላስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

@minster_of_education
2.0K views03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 06:14:33
#Update

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡ ተማሪዎች የካቲት 15 እና 16/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ፦

➧ በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣
➧ በላምበረት መናኸሪያ፣
➧ በአቃቂ መናኸሪያ እና
➧በአስኮ መናኸሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡

@minster_of_education
1.9K views03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 06:14:20
#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ የካቲት 15 እና 16/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
 
በየተመደባችሁበት ካምፓሶች ለምዝገባ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ (8)፣
➧ ብርድልብስና አንሶላ፣
➧ የስፖርት ትጥቅ።

ከተገለጹት ቀናት በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት #እንደማይሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

➤ በአዲስ አበባ የምትኖሩ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት ➧የካቲት 17/2015 ዓ.ም

➤ የመልሶ ቅበላ አመልካቾች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ
➧ከየካቲት 15 እስከ 17/2015 ዓ.ም

@minster_of_education
1.9K views03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 06:13:59
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ92 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን የተማሪዎች መኖሪያ ህንፃ አስመርቋል።

ሦሥት ብሎኮችን የያዘው ባለ አራት ወለል ህንፃ፤ ከ1 ሺህ 200 በላይ ተማሪዋችን የማስተናገድ አቅም አለው ተብሏል።

ህንፃው በተያዘው የትምህርት ዘመን ዩኒቨርሲቲውን የሚቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎችን የሚያስተናግድ መሆኑ ተገልጿል።

ህንፃው የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል መሆኑ ተመልክቷል።

@minster_of_education
1.8K views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 06:13:45
በሲዳማ ክልል በ2014 የትምህርት ዘመን በተመዘገው ዝቅተኛ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

በክልሉ 53 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው፤ ውጤት ያመጡት 2 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ ናቸው።

“ትምህርት ቤቶች ያሉበት ደረጃ ደካማ መሆን፣ የተማሪዎች ተነሳሽነት ማነስ፣ የመምህራን እጥረት እንዲሁም የትምህርት አመራሩ ቁርጠኝነት ማነስ” ለተማሪዎቹ ውጤት ማጣት ተጠቃሽ ምክንያት መሆናቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሶ አንስተዋል።

በክልሉ የተሻለ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎችን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሠራ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በሃዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የማካካሻ ትምህርት ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

@minster_of_education
2.1K views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 22:48:51
ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜው ነገ ያበቃል!

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁና በወጪ መጋራት ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ያላችሁን ማንኛውም ቅሬታ እስከ ነገ የካቲት 07/2015 ዓ.ም 6፡00 ድረስ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ምንም አይነት ማመልከቻም ሆን ቅሬታ በአካል እንደማይቀበል መግለጹ ይታወቃል።

ከምደባው ጋር ተያይዞ ጥያቄ ያላችሁ ተማሪዎች placement.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።

@minster_of_education
459 views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 21:02:14
#Update

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በወጪ መጋራት ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ይታወቃል።

ውጤት ያመጡ 30,004 ተማሪዎች በ15 ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ታውቋል (ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።)

ብዙ ተማሪዎች የተመደቡባቸው ቀዳሚ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች፦

➧ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (5,187)፣
➧ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (4,950)፣
➧ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (2,337)፣
➧ ጅማ ዩኒቨርሲቲ (2,309) እና
➧ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (1,796)

@minster_of_education
1.4K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 14:12:12
#Update

በአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የተካተቱ ተማሪዎች በቀጣይ ቀናት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም/ዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን የደርጋሉ፡፡

በተማሪዎቹ ምርጫ መሠረት የዩኒቨርሲቲ/የተቋም ምደባ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚደረግ ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ሰምቷል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ለአራት ወራት ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ይሰጣል መባሉ አይዘነጋም፡፡

@minster_of_education
2.7K views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 12:07:02
#Update

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ  የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

(የአቅም ማሻሻያ የመቁረጫ ነጥቡን ከላይ ይመልከቱ)

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@Minster_of_education
3.0K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ