Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
ርዕሶች ከሰርጥ:
Moe
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
ርዕሶች ከሰርጥ:
Moe
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.50K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-02-13 14:12:12
#Update

በአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የተካተቱ ተማሪዎች በቀጣይ ቀናት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም/ዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን የደርጋሉ፡፡

በተማሪዎቹ ምርጫ መሠረት የዩኒቨርሲቲ/የተቋም ምደባ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚደረግ ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ሰምቷል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ለአራት ወራት ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ይሰጣል መባሉ አይዘነጋም፡፡

@minster_of_education
2.7K views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 12:07:02
#Update

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ  የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

(የአቅም ማሻሻያ የመቁረጫ ነጥቡን ከላይ ይመልከቱ)

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@Minster_of_education
3.0K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 12:06:49
#የመቁረጫ_ነጥብ

የአቅም ማሻሻያ (ረሜዲያል) የመቁረጫ ነጥብ፦

- የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 263

- የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 227

- የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 220

- የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 190

- የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 210

- የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 210

- የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 180

- የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 180

(ተጨማሪ ከላይ በተያያዘው ምስል ያንብቡ)

@Minster_of_education
2.8K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:01:53
#MoE

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያረጋገጠውና ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተላከ ደብዳቤ፦

➤ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን ነሐሴ አጋማሽ ላይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ታቅዷል።

➤ የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እስከ ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ ታሳቢ ተደርጓል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በመንግስት የኒቨርሲቲዎች የሚደለደሉትንና በራሳቸው ወጪ በመሸፈን በግል የሬሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን በተመለከተ፦

➤ የሬሚዲያል ፕሮግራም ለአራት ወራት ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ታቅዷል።

➤ የሬሚዲያል ፕሮግራም በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ በሁለት መስክ ተከፍሎ ከማዕከል በተዘጋጀ ይዘት መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ የሚያክሉትን በማካተት በተዘጋጀው መነሻ መሰረት ፕሮግራሙ እንዲከናወን ታቅዷል።

➤ የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 በመቶ እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70 በመቶ ተመዝነው በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ በቆዩበት ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል።

(ተጨማሪውን ከላይ ከተያያዘው ደብዳቤ ያንብቡ፡፡)

@Minster_of_education
2.1K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:01:37
የገንዘብ ድጋፍ በሚያስገኝ ውድድር ይሳተፉ!

ትምህርት ሚኒስቴር እና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከብሪታንያ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (UKaid) ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር (University Industry Linkage) ላይ መሰረት ያደረጉ ችግር ፈቺና ወደ ኢንዱስትሪው ሊሸጋገሩ የሚችሉ የተጠናቀቁ የምርምር ውጤቶችን አወዳድሮ ወደ ገበያ እንዲገቡ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግ ውድድር ይፋ አድርገዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት፣ በምርምር ማዕከላት እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየሩ የሚችሉ እና ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የምርምር ውጤቶች ያላችሁ እና የመወዳደሪያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለሙያዎች በውድድሩ መሳተፍ ትችላላችሁ።

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ የካቲት 11/2015 ዓ.ም

ለማመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://forms.gle/ESk1iYwf9bYhJo879

ለበለጠ መረጃ፦

0948862349 ወይም 0912612679

E-mail፦

teshome.daniel@ethernet.et
atirenegash@gmail.com

@Minster_of_education
907 views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:01:25
በጣልያን የሙሉ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ ይሁኑ!

የጣልያን መንግስት በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ሙሉ ስኮላርሺፕ ሰጥቷል።

የስኮላርሺፑ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ በ @rasbitwededservices ያነጋግሩን።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ፦

https://t.me/+f1BRMl9qxWYxYjdk

ለተጨመሪ መረጃ፦

0964826768 / 0944442700

አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ሽመክት ህንጻ፣ 10ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 08
758 views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:01:19
ክቡር ኮሌጅ በአራት የትምህርት ዘርፎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለመስጠት ሙሉ እውቅና አግኝቶ በ2015 ዓ.ም ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ መጀመሩን እናበስራለን፡፡

TVET Programs:

1. Hardware and Networking Service (Level I-IV)
2. Web Development and Database Administration (Level I-IV)
3. Marketing and Sales Management (Level II-IV)
4. Accounting and Finance (Level II-IV)

ምዝገባ ጀምረናል!

Website: https://kibur.edu.et

አድራሻ:- ጀሞ መካኒሳ ሚካኤል ከአፍሪካ ህንፃ አጠገብ

0113854042 / 0904848586

Telegram: https://t.me/kiburcollege
Facebook: https://www.facebook.com/kiburcollege
659 views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:01:05
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ያተኮረ የትምህርት ክፍል ሊያቋቁም ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ያተኮረ የትምህርት ክፍል ለማቋቋም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

ኮሌጁ ዘጠኝ የትምህርት ክፍሎችን ያሉት ሲሆን በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ያተኮረ አሥረኛ የትምህርት ክፍል ለማቋቋም ፕሮጀክት ቀርጾ ዝግጅት መጀመሩን የኮሌጁ ዲን ደበበ ኤሮ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

የትምህርት ክፍሉ መቋቋም ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ለመንግስት እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንዲሁም የምርምር ድጋፍ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

@Minster_of_education
577 views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:00:46
#ማስታወሻ

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያመጣችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን የማስተካከያ ጊዜ ዛሬ የካቲት 03/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እንድታስተካክሉ በትምህርት ሚኒስቴር #የተራዘመው የጊዜ ገደብ ዛሬ 12፡00 ሰዓት ይጠናቀቃል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁንና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አትዘንጉ
https://student.ethernet.edu.et

@Minster_of_education
562 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:00:37
Do you want to buy or sell items online?

Do you need price information and other data about different products?

Https://www.ishururu.com has got you covered.

We have listed:

Slightly used laptops starting from 15,000 Birr
New smartphones starting from 15,000 Birr

And much more …..
All the data is available on our Telegram channel @ishururu
558 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ