Get Mystery Box with random crypto!

በሲዳማ ክልል በ2014 የትምህርት ዘመን በተመዘገው ዝቅተኛ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ላይ | MINSTER OF EDUCATION

በሲዳማ ክልል በ2014 የትምህርት ዘመን በተመዘገው ዝቅተኛ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

በክልሉ 53 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው፤ ውጤት ያመጡት 2 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ ናቸው።

“ትምህርት ቤቶች ያሉበት ደረጃ ደካማ መሆን፣ የተማሪዎች ተነሳሽነት ማነስ፣ የመምህራን እጥረት እንዲሁም የትምህርት አመራሩ ቁርጠኝነት ማነስ” ለተማሪዎቹ ውጤት ማጣት ተጠቃሽ ምክንያት መሆናቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሶ አንስተዋል።

በክልሉ የተሻለ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎችን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሠራ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በሃዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የማካካሻ ትምህርት ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

@minster_of_education