Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-03-04 22:50:44
#InjibaraUniversity

በ2015 ዓ.ም በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መጋቢት 4 እና 5/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀምረው ➧ መጋቢት 6/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ
➧ አጋዥ የትምህርት መጻሕፍት፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.1K views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:50:32
#DebarkUniversity

በ2015 ዓ.ም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መጋቢት 5 እና 6/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በቅጣት የመመዝገቢያ ጊዜ ➧ መጋቢት 7/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ
➧ ማጣቀሻ መጻሕፍት፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.1K views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:50:20
#BongaUniversity

በ2015 ዓ.ም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 1 እና 2/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➧ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.1K views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:50:09
#AssosaUniversity

በ2015 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 11 እና 12/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ውጤት፣
➧የትምህርት ማስረጃዎች፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት።

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@Minster_of_education
1.1K views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:49:51
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ለትምህርት ቤቱ የሚውለው ወጪ ሙሉ ለሙሉ የሚሸፈነው ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ይልማ ታዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

"ወጪው በደቡብ ክልል መንግስት እና ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋራ እንደሚሸፈን" በመገናኛ ብዙሃን የተገለጸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ ሙሉ ወጪ በሰዎች ለሰዎች ድርጅት እንደሚሸፈን አረጋግጠዋል።

በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም የተቋቋመው ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) ላለፉት 40 ዓመታት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

@Minster_of_education
1.1K views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:49:35 ለተጨማሪ ትክክለኛ መረጃ የተቋማትን አድራሻ ይከተሉ ፦

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

https://www.facebook.com/100064506646894/posts/pfbid02DVPdfpmYVcbfq7JRoqDYjyLEhowpZ2WcNj3t7gGwtTwURjhiTcVHH8Ud5bbNwciZl/?app=fbl

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር
https://www.facebook.com/100066354648770/posts/pfbid0LVKs2N1zg487tUtgcNKzfYLZDKQe1VKJHQruZCiq7Csm5RpyM19gkHqKwRsh3wDEl/?app=fbl

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
 https://www.facebook.com/100068345581900/posts/pfbid02DBUptazWEyJ24hHt2v2HGCAEy5cKbK7WLAGGhgaXopG2zp6FBMyDd6C5LaE981jfl/?app=fbl

ወሎ ዩኒቨርሲቲ

https://www.facebook.com/100064843324907/posts/pfbid02oae5M8FAd9YRkYsTpQxQTh9dFCBvVyh5CkRA68F4WHRBoy2pE7hPKicGhPC6MDCZl/?app=fbl

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02NM1JzyHcchg3BqBhCy6ErkngFJhRSS3EN47ei8eGoqZmoJVY1Kgm8JpfqeSLhc73l/?app=fbl

@Minster_of_education
1.1K views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:49:22
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ ፦

በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ /Remedial Program/ ፕሮግራም ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ / ምዝገባ ቀን ፦

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ ከየካቲት 30/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 01/2015
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ መጋቢት 4 እና 5 ቀን 2015 ዓ/ም (መጋቢት 6 ትምህርት ይጀምራል)
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - መግቢያ ቀን መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2015 ዓ/ም
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ መጋቢት 1 እና 2 / 2015 ዓ/ም
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ - ምዝገባ መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም በቅጣት መጋቢት 7
ወሎ ዩኒቨርሲቲ - መግቢያ ቀን መጋቢት 4 እና 5 ቀን 2015 ዓ/ም

@Minster_of_education
1.0K views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 20:12:31
#Update #UAE

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ በተለይ " ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁ " ብለዋል።

#ኤፍቢሲ

@Minster_of_education
2.1K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 14:09:40
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ መደበኛ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ የካቲት 20 እስከ 21/2015 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

መንግስት ከ1 ሺህ 300 በላይ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መመደቡ ይታወቃል።

@minster_of_education
2.8K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 14:09:25
#HawassaUniversity

በ2015 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከየካቲት 30/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 01/ 2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ምዝገባ የማድረጊያ ቦታዎች ➧

በ Social Science የተመደባችሁ የስም ፊደል ከ A-L በቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት ግቢ፤ የስም ፊደል ከM-Z በዋናው ግቢ፡፡

በ Natural Science የተመደባችሁ የስም ፊደል A-E በበንሳ ዳዬ ግቢ፤ የስም ፊደል ከF-P በግብርና ኮሌጅ ግቢ እንዲሁም የስም ፊደል R-Z በዋናው ግቢ፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ (4) ፣
➧ የሌሊት አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከተጠቀሱት ቀናት በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን የማያስተናግድ መሆኑን አሳስቧል።

@minster_of_education
2.7K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ