Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-06 10:24:47
#JimmaUniversity

በ2015 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 29 እና 30/2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ10ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

የተመደባችሁበትን ካምፓስ ለማየት ተከታዩን ሊንክ ተጠቀሙ ➧ https://portal.ju.edu.et

@Minster_of_education
3.2K views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 21:06:46
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በጎረቤት ሶማሊላንድ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው በሶማሊላንድ ከሚገኘው ጎሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል።

በስምምነቱ መሠረት ከመጋቢት 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሶማሊላንድ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በስትራክቸራል ምህንድስና የትምህርት ዘርፍ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ገልጿል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሀገር ውጪ ትምህርት ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

@Minster_of_education
1.6K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 21:06:39
ልዩ ስልጠና ለ12ኛ ክፍል የማጠናከሪያ ትምህርት (Remedial Program) ለሚወስዱ ተማሪዎች!

ውጤታማ የጥናት ክህሎት       
የፈተና አሰራር ጥበብ
የጊዜ አጠቃቀም ክህሎት          
የእችላለሁ አስተሳሰብ ማሳደግ

ስልጠናው በዘርፉ ጥናት ባደረጉ፣ መጻሕፍት ባሳተሙ እና በቂ ልምድና ብቃት ባካበቱ አሰልጣኞች ይሰጣል፡፡

ስልጠናው ለሦሥት ቀናት ይሰጣል፡፡           
የስልጠናው ክፍያ 500 ብር
ምዝገባ የካቲት 28/2015 ዓ.ም ያበቃል፡፡
ስልጠናው የካቲት 29/2015 ዓ.ም ይጀምራል፡፡
በኮሌጃችን የብቃት ማሻሻያ የሚወስዱ ተማሪዎች ከክፍያ ነፃ ናቸው፡፡
ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

አሰልጣኞች፡-

➧ አሰልጣኝ አየናቸው ጥሩነህ (ILO National Certified Trainer)
➧ አሰልጣኝ እቴነሽ ተስፋ (ግላዊና ሙያዊ ልህቀት አሰልጣኝ)

ምዝገባ ጀምረናል!             ክቡር ኮሌጅ!

አድራሻ:- መካኒሳ /ጀሞ ሚካኤል ከአፍሪካ ህንፃ አጠገብ

         0113854042 / 0904848586
Telegram: https://t.me/kiburcollege
Facebook:  https://www.facebook.com/kiburcollege
1.5K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:52:10
#OdaBultumUniversity

በ2015 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 4 እና 5/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣

➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣

➧ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣

➧ 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (4)፣

➧ የሌሊት አልባሳት፣

➧ የስፖርት ትጥቅ።

ዘንድሮ የአንደኛ ዓመት ማሪዎች ዳግም ቅበላ እንደማይኖር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@Minster_of_education
2.1K views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:51:59
#ArbaMinchUniversity

በ2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀን የካቲት 29/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቀናት➧የካቲት 30 እና መጋቢት 1/2015 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀምረው➧ መጋቢት 4/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና 2 ኮፒ፣

➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣

➧ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና 2 ኮፒ፣

➧ ፓስፖርት መጠን 2 ፎቶግራፍ፣

➧ የሌሊት አልባሳት፣

➧ የስፖርት ትጥቅ፣

➧ የአፍ መሸፈኛ ማስክ።

የምዝገባ ቦታ፦

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ➧ በአባያ ካምፓስ

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ➧ በጫሞ እና ሳውላ ካምፓሶች

የተመደባችሁበትን ካምፓስ፣ የመማሪያ ክፍል እና የተማሪ መለያ መታወቂያ ቁጥር ዝርዝር መረጃ ከዩኒቨርሰቲው ድረ-ገጽ www.amu.edu.et እና የፌስቡክ ገጽ ማግኘት ይቻላል።

https://t.me/arbaminch_university/10022

@Minster_of_education
1.6K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:51:46
#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል አከባበር የፕሮጀክት ማስተዋወቂያ ልዩ መርሃ ግብር እያከናወነ ይገኛል።

በመድረኩ የዩኒቨርሲቲውን የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ በባህር ዳር ከተማ የሚገነቡ አምስት ፕሮጀክቶች ተዋውቀዋል፦

➧ አብርሆት በባህር ዳር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት

➧ ባህር ዳር የከተማ ብስክሌት ፕሮጀክት

➧ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ፓርክ ፕሮጀክት

➧ ሞዴል ትምህርት ቤት

➧ ጣና የጤና ምርምር ማዕከል

ባለሀብቱ በላይነህ ክንዴ አብርሆት በባህር ዳር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ፕሮጀክትን ሙሉ ወጪ እንደሚሸፍኑ ቃል ገብተዋል።

በመድረኩ የሚገነባው ቤተ መጻሐፍት "በላይነህ ክንዴ" የህዝብ ቤተ መጻሕፍት ተብሎ እንዲሰየም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

@Minster_of_education
1.4K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:51:40
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮ የትምህርት ዘመን 1 ሺህ 780 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ተመድበውለታል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ 600 ተማሪዎችንም እየተቀበለ ነው፡፡

@Minster_of_education
1.3K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:51:24
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 76 ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።

21 ተማሪዎች ከ600 በላይ፣ 45 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት እንዲሁም 10 ተማሪዎች ከ400 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ትምህርት ቤቱ በዚህ ዓመት በአዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ከ600 በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል።

@Minster_of_education
1.2K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:51:08
#WolaitaSodoUniversity

በ2015 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 1 እና 2/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀመረው ➧ መጋቢት 4/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ መሰናዶ ያለፋችሁበት ሰርተፍኬት፣
➧ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.2K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 22:50:57
#woldiaUniversity

በ2015 ዓ.ም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ የካቲት 30 እና መጋቢት 1/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.2K views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ