Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-03 00:07:48
በ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ የህጋዊነት ማረጋገጫ ተደርጎ 900 የሚሆኑት ሐሰተኛ ሆነው ተገኙ።

የትምህርት ማስረጃዎቹ ተመሳስለው የተሠሩ፣ ዕውቅና ከሌለው ተቋም የተሰጡ፣ ባልተፈቀደ የሙያ መስክ የሰለጠኑ እንዲሁም የመቁረጫ ነጥብና የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው የሠለጠኑ መሆናቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለሥስልጣን አሳውቋል።

የተወሰኑ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባለሥልጣኑ ዕውቅና ውጪ ካምፓስ አስፋፍተውና ፍቃድ ባላገኙበት የትምህርት ዘርፍ ስልጠና ሲሰጡ መገኘታቸውንም ባለሥስልጣኑ አረጋግጧል።

ባልተፈቀደላቸው የትምህርት መርሃ ግብር እና ከተቀመጠላቸው ቁጥር በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው ሲያስተምሩ የነበሩ ተቋማት መገኘታቸውንም የባለሥስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሽፈራው ሽጉጤ ገልጸዋል።

@Minster_of_education
1.0K views21:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 12:42:29
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎች ተቀብሏል።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር ለተመደቡለት ከ2 ሺህ 9 መቶ በላይ የሪሚዲያል ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

@Minster_of_education
1.8K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 12:42:08
የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም በክልሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ሰጥቷል።

በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ትምህርት ቤቶችም ዕውቅና ተሰጥቷል።

በደቡብ ክልል በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 2.6 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸው ይታሳል።

@Minster_of_education
1.8K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 12:41:31
#Online_Opportunity

በተባበሩት መንግስታት የኦንላይን በጎ ፍቃድ ፕሮግራም (UNOVP) ይሳተፉ!


➭ ሙሉ ወጪ የሚሸፈንበት
➭ ምንም የማመልከቻ ክፍያ የማይጠይቅ
➭ በኦንላይን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥበት
➭ በጎ ፍቃደኞች በፈለጉት መስክ የመምረጥ ዕድል ያገኛሉ

ፕሮግራሙ በጎ ፍቃደኞች ከዓለም አቀፍ ታዋቂ ተቋማት ጋር የመስራት፣ ሥራዎቻቸውን ለማሳየት እና ትስስር ለመፍጠር ዕድል ያስገኛል።

ምዝገባው በመካሄድ ላይ የሚገኝ

ለማመልከት ➭ https://tinyurl.com/38m4y28x

@Minster_of_education
1.7K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 15:12:18
አራት የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው እንዳለፈ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትላንት መጋቢት 09/2015 ዓ.ም በደረሰ የመኪና አደጋ የአራት ተማሪዎቹ ህይወት ማለፉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ስለ አደጋው ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም፤ "አደጋው የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ልብ የሰበረና አስደንጋጭ ድንገተኛ ክስተት መሆኑን" ጠቁሟል።

"አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መሪር ሀዘን ላይ መሆኑንም" አመልክቷል።

በአደጋ ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች ሦሥቱ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ሲሆኑ አንዱ የአራተኛ አመት ተማሪ መሆናቸው ተገልጿል።

በአደጋ ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች ደሳለው ፈጠነ፣ በላይ አንዱዓለም፣ አቸነፍ አሰፋ እና በላቸው አሳየ መሆኑን ተቋሙ አረጋግጧል።

@Minster_of_education
1.8K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 15:10:09
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የጠራው ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ሊሰጥ በታሰበው የመውጫ ፈተና ዙሪያ በስሙ የተሰራጨው መረጃ ህብረቱን የማይወክል መሆኑንም ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

በዚህ ዓመት እንዲሰጥ በተወሰነው የመውጫ ፈተና ላይ ተማሪዎች በሚያነሷቸው ስጋቶችና ቅሬታዎች ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች መደረጋቸውን ወደፊትም እንደሚደረጉ ህብረቱ ገልጿል።

በውይይቶቹ የተነሱ ሀሳቦች ገሚሶቹ ምላሽ ያገኙ ሲሆን በቀጣይ የሚስተካከሉ መረጃዎችን የሚያሳወቅ መሆኑንም ህብረቱ ጠቁሟል።

ፈተናው የተማሪዎችን ብቃት የሚመዝንና የትምህርት ጥራት ሊያስጠብቅ በሚችልበት ሁኔታ ላይ አሁንም በጋራ እየሠራ መሆኑን ህብረቱ አስታውሷል።

ተማሪዎች በፈተናው እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሀሳብ በግቢያቸው ለሚገኙ የተማሪዎች ህብረት እያቀረቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አማካይነት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመወያየት ምላሽ የሚሰጥበት መሆኑንም ገልጿል።

በቅርቡ የተሰራጨው መረጃ ህብረቱን የማይወክልና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጸው ህብረቱ፤ በህብረቱ የተጠራ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

ተመራቂ ተማሪዎች በተቋሞቻቸውና በተማሪዎች ህብረት አማካይነት የሚሰጡ የድጋፍ ትምህርቶችን በመከታተል ለመውጫ ፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ህብረቱ ጥሪ አድርጓል።

ሐሰተኛና የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ህብረቱ አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.7K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 15:09:31
የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር አማኑኤል ባልቻና ቡድኑ ተጨማሪ ድሮኖች ሰርተው የሙከራ በረራ ማድረጋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የሙከራ በረራዎቹ የተሳኩ እንደነበሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የመምህር አማኑኤል ባልቻ ቡድን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ15 በላይ ድሮኖችን መስራታቸው ተገልጿል፡፡

@Minster_of_education
1.6K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 15:08:23
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የተመደቡ አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዛሬ መጋቢት 11/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

@Minster_of_education
1.7K views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 18:57:12
#GambellaUniversity

በ2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ መጋቢት 08 እና 09/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@Minster_of_education
2.2K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 13:47:27
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል የትምህርት ፕሮግራም በተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ እንደሚያደርግ ግልጿል፡፡

ተቋሙ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በቅርቡ እንዳጠናቀቀ በይፋ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ የሚዲያ ገጾቹ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽ www.du.edu.et ጥሪ የሚያደርግ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ በተቋሙ የተመደባችሁ ተማሪዎች በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

@Minster_of_education
2.3K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ