Get Mystery Box with random crypto!

#AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 5 ሺህ 100 አዲስ ገቢ ተማሪ | MINSTER OF EDUCATION

#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 5 ሺህ 100 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲተው በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ 5 ሺህ 100 ተማሪዎችን ከዛሬ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይቀበላል፡፡

ከአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ መካከል 3 ሺህ 51 በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተመደቡ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ሽብሩ ተመስገን (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በ11 ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ይታወቃል፡፡

@minster_of_education