Get Mystery Box with random crypto!

የምርምር እና የፈጠራ ሥራዎቻችሁን ያቅርቡ! የትምህርት ሚኒስቴር በቀጣይ ወር በሚያዘጋጀው ሀገር | MINSTER OF EDUCATION

የምርምር እና የፈጠራ ሥራዎቻችሁን ያቅርቡ!

የትምህርት ሚኒስቴር በቀጣይ ወር በሚያዘጋጀው ሀገር አቀፍ አወደ ጥናት እና አውደ ርዕይ ላይ የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ተቋማት የምርምር እና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን እንድታቀርቡ ጋብዟል፡፡

ሚኒስቴሩ ከፌደራል የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ‘’የኢትዮጵያ ምርምር ስነ-ምህዳር፣ ተግዳሮቶች እና ተስፋዎች’’ በሚል ጭብጥ ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የምርምር አውደ ጥናት እና አውደ ርዕይ ከመጋቢት 28-30/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ያካሂዳል፡፡

የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሚታደሙበት መድረክ፤ የምርምርና ፈጠራ ሥራዎች በተመረጡ የከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ተቋማት ለዕይታ ይቀርባሉ፡፡

ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው የምርምር እና የፈጠራ ውጤቶች ያሏችሁ ተቋማት እስከ የካቲት 25/2015 ዓ.ም ድረስ የምርምር ፈጠራውን ስም፣ የተሰራበትን ተቋም እና ጊዜ እንዲሁም የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በጽሑፍ እና በምስል በማስደገፍ ለ tesfamariam.shimekit@ethernet.edu.et መላክ ትችላላችሁ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ➧ 0912887336

@minster_of_education