Get Mystery Box with random crypto!

ወደፊት የሚቋቋሙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች 'ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ' የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋ | MINSTER OF EDUCATION

ወደፊት የሚቋቋሙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ" የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የውይይት መድረክ የትምህርት ሚኒስትር
ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የማድረጉ ሂደት በተያዘው ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሮ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ በስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።

“መስፈርቱን አሟልተው የሚፈጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲኖሩ"፤ አዋጁ ወደፊት የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎችንም የሚመለከት መሆኑን ዶ/ር ሳሙኤል አስረድተዋል።

ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከፍለው የሚማሩ መሆን እንዳለባቸውም ዶ/ር ሳሙኤል አመልክተዋል።

“ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ አይመደብላቸውም” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፤ ፍትሃዊነትን ለማምጣት ሙሉ እና ከፊል-ነጻ የትምህርት ዕድል ለተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

ረቂቁ “ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እና አካዳሚያዊ ተወዳዳሪነት” ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ከሚያበቁ መስፈርቶች መካከል እንደሚካተቱ ይጠቅሳል።

ለዚህም “ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኳቸው ውጤታማ ለመሆን ሀብት ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው።

ሀብት ለማመንጨት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎቹ “የንግድ ድርጅት ሲያቋቁሙ፤ ሌላ ነጋዴ መስራት የሚችለውን ሳይሆን ከተልዕኳቸው ጋር የሚመጋገብ” መሆን እንዳለበት ዶ/ር ሳሙኤል አስረድተዋል፡፡

@Minster_of_education