Get Mystery Box with random crypto!

የሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወ | MINSTER OF EDUCATION

የሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚችሉ ተገለፀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበን ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ሚያዝያ 17/2015 ዓ.ም አጽድቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸው እና የሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ እንደሚችል በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) በመድረኩ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አባላት የሚሆኑ ከሆነ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የሕ/ተ/ም/ቤት

@minster_of_education