Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉትን ዝግጅቶች ማጠናቀቁን አሳውቋል | MINSTER OF EDUCATION

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉትን ዝግጅቶች ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው "ራስ ገዝ" ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ገልጸዋል፡፡

በዚህም የፋይናንስና የሰው ኃይል አደረጃጀት መመሪያ ተዘጋጀቶ ከሰራተኞች ጋር ውይይት መደረጉንና መመሪያው በቀጣይ ለቦርድ ውሳኔ የሚቀርብ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ለኢዜአ ተናግረዋል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውይይት እየተደረገበት ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የአዋጁን መጽደቅ እየጠበቀ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆን የአካዳሚ፣ የአስተዳደር፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር ተገልጿል።

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የምርምር ተልዕኮ የተሰጣቸውና የመጀመሪያው ትውልድ ተብለው የተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝ" እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

@Minster_of_education