Get Mystery Box with random crypto!

'በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ ይጀመራል።' የትምህርት ሚ/ | MINSTER OF EDUCATION

"በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ ይጀመራል።"

የትምህርት ሚ/ር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በአገር አቀፍ ደረጃ ከ47 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አዲስ ወግ በተሰኘ የውይይት መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተገቢውን መስፈርት ባሟላ መልኩ የተገነቡ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።

በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ዘመቻ ለማከናወን ዕቅድ መዘጋጀቱን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዘመቻው በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ አካባቢዎች የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት እንደሚሰራም ሚኒስትሩ መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል፡፡

@Minster_of_education