Get Mystery Box with random crypto!

ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

የሰርጥ አድራሻ: @man_united_ethio_fans
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282.39K
የሰርጥ መግለጫ

👉 ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ቻናል ነዉ። ይህ ቻናል ስለ ውዱ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደ እናንተ ያደርሳል።
ለማንኛዉም አስተያየት
@wizhasher
@wiz_hasher
Group 👉 @Man_United_ethio_fans_Group
{ስልክ ቁጥር}
0912983847
0919337648

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 527

2022-08-31 22:04:53
ፋብሪዚዮ ሮማኖ ስለ ክለባችንን ይቀላቀላሉ እየተባሉ የሚገኙት ቪክቶር ኦስሚሄን እና ሰርጂዮ ደስት ያወጣው መረጃ...

በማንችስተር ዩናይትድ እና በቪክቶር ኦሲምሄን ዙሪያ ምንም ነገር የለም እና ቪክቶር ኦስሚሄን ወደ ዩናይትድ ስለመዘዋወሩ የሚናፈሰው ወሬ ሁሉም ውሸት ነው።

ለእንግሊዛዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ አሮን ዋን ቢሳካ ማን ዩናይትዶች የሚፈልጉት ምንም አይነት ጥያቄዎች ስለሌለ ይህ ተከላካይ በዩናይትድ እንደሚቆይ ይጠበቃል። ስለዚህ ሰርጂዮ ደስት ወደ ኦልትራፎርድ በመዘዋወር ላይ አሁን ላይ ምንም አይነት መሻሻል አልታየም።

[Fabrizio Romano]

@Kareem_Abuki
@man_united_ethio_fans
26.0K views𝐊𝐀𝐑𝐄𝐄𝐌 𝐀𝐁𝐔𝐊𝐈 , 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:50:28
አይቮሪኮስታዊው አማካኝ አማድ ዲያሎ በውሰት የሻምፒዮን ሺፑን ክለብ ሰንደርላንድን ለመቀላቀል ተቃርቧል!!

በማንችስተር ዩናይትድ እና በሰንደርላንድ መካከል የሚደረገው ድርድር ከስምምነት ለመድረስ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች በአንድ አመት የውሰት ውል ነው እየተደራደሩ ያሉት።

[Laurie Whitwell]

@Kareem_Abuki
@man_united_Ethio_fans
26.5K views𝐊𝐀𝐑𝐄𝐄𝐌 𝐀𝐁𝐔𝐊𝐈 , edited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:38:03
አንቶኒ እንግሊዛዊ ቢሆን ኑሮው 100 ሚሊዮን ዩሮ The most underrated Player ያስበለው ነበር ብራዚላዊ ስለሆነ ብቻ...የእንግሊዝ ሚዲያ ኦቨሬትድ በሚል ቃል ተወጥሯል...

አያክስ ከዝውውሩ ምን ያህል ያገኛል...አስቡት በፓወንድ ቢሆን 80ቤት ይገባል የአንቶኒ የዝውውር ሂሳብ በዩሮ ስለሆነ ነው 100 ቤት የገባው....

የአንቶኒ የቀድሞ ክለብ ሳኦ ፓውሎ አንቶኒን ለአያክስ ሲሸጥ አንድ ውል አካቶ ነበር አያክስ አንቶኒን መልሶ የሚሸጠው ከሆነ ከተጫዋቹ ዝውውር 15% የሚሆነው ከተጫዋቹ የሚገኘው ገንዘብ ለሳኦ ፓውሎ ግቢ ይሆናል የሚል ውል አካቶ ነበር !

ወኪሉም ከዝውውሩ ላይ የሚያገኘው ገንዘብ አለ አያክስ እንደ ክለብ ተጠቃሚ መሆን ስለሚፈልግ እና ቢያንስ መስጠት ያለበትን ሰቶ ጥሩ የዝውውር ሂሳብን ማገኘት ሰለሚፈልጉ ነው የዝውውሩ ጉዳይ ውስብስብ ሆኖ ለቀናት የቆየው !

ሲቀጥል ክለባችን ከነበረበት የውጤት ቀውስ አንፃር እንዲሁም ደግሞ በቻምፒየንስ ሊጉ ካለመሳተፋችንም አንፃር ተገቢ የሆነ የዝውውር ሂሳብ ነው እላለሁ በግሌ..እግርኳሳዊ በሆነ መንገድ ካየነው ግልፅ ነው ተጫዋቹ ከተጣለበትም ተስፋ አንፃር

እኔ የምሰገው ደጋፊው የሚጠብቀው HIGH EXPECTATION ተጫዋቹን እንዳይጎዳው ነው በተረፈ በተጫዋቹ በቃት አልጠራጠርም !

ኤላ

@Elias_Wazza
@man_united_ethio_fans
27.7K viewsᴇʟɪᴀs ᴡᴀᴢᴢᴀ, edited  18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:32:06
አስተኳሹ ዌንገር...

ያንን የ90 ደቂቃ ፍልሚያ ምናልባትም ፈረንሳያዊዉ ሰው አርሴን ዌንገር ፈፅሞ ሊያስቡት አይፈልጉም ይሆናል... በፕሪሚየር ሊጉ ድንቅ ግስጋሴ ላይ የነበረውን አርሰናልን እና የክለቡን ጉምቱ በረኛ የዴቪድ ሴሞንን መረቦች አንድ ነጭ የ17 አመት እንቦቃቅላ ይደፍረዋል ብሎ ማን ጠበቀ...በዚህ እድሜኮ አንድ እንግሊዛዊ ቤቱ ቁጭ ብሎ ስለ ሳይንስ ፈተናው የሚያስብበት ወቅት ነው! ይህ ሰው ግን በዚህ እድሜው በ2002 የአርሰን ዌንገርን ጦር ድባቅ በመምታት ፊቱን ብሎም ረጃጅም ተምዘግዛጊ ቅልጥሞቹን ለአለም አስተዋወቀ።

ዌንገር የመቆጣት ስሜት ፊታቸው ላይ ይነበባል... ነገርግን በቅፅበት ስለ ነጩ ኮከብ አስተያየታቸውን በሚሰጡበት ወቅት ታዳጊው ላይ የሩቅ ተስፋ አብሪ ኮከብነት የሰነቀ ትንቢት ቢጤ ጣል አደረጉ!

" ይህ ልጅ ግሩም ነው! ወደፊት በትልቅ ደረጃም እንደማየው እርግጠኛ! ነኝ አሉ። ከዛ ጨዋታ በኋላ ነበር ዌንገር ሮኒን ለማስፈረም ያለመታከት መድከም የጀመሩት።

ግና የግልፍተኛው ወጣት አይን ለንደንን አልመረጠም... ሪፐብሊክ ኦፍ ማንቹሪያን የዋዛ ድንቅ ምርጫ ሆኖ ቀረ። ወትሮውኑ ግልፍተ አመል ያለባቸው ታዳጊዎች መልበሻ ቤት ከመበጥበጥ ባለፈ ታላቅ አንድምታ ከበስተጀርባቸው አለ ብለው የሚያምኑት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እየመረራቸውም ቢሆን ጣፋጩን ሮኒን ለማግኘት ወሰኑ...ከዴቪድ ቤካም እና ንጉሡ ካንቶና ተመሳሳይ መንገድ ትእግስታቸውን ቢፈታተናቸው እንኳን ወደፊት የሚያሳየው ትንታግ ሃይል ለቡድኔ ይጠቅማል በማለት ዋይን ሩኒን በዚህች ቀን አስፈርሙ...።

[ሚካኤል]

@Micky_united
@Man_united_ethio_fans
26.4K viewsጃል ሚካኤል ᴊʀ, 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:26:31 [#የቀጠለ]

በመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች የቡድኑ ከፍ ማለት በተመሳሳይ ተጨዋቾች ላይ ያሳደርከዉ የሁኔታ ፣ የዝግጁነት ፣ የመነሳሳት ለዉጥ ነዉ ?

" ይህን እንደ ጅማሮ ነዉ ማየዉ ፤ አሁን ጥሩ መሰረት አለን ብዬ አስባለዉ ነገር ግን ይህ እኛ ማምጣት ከምንፈልገዉ ትንሹ ነዉ። ይህንን መነሳት በማየቴ ደስተኛ ነኝ እናም ይህንን መንፈስ እና የማሸነፍ ስነ ልቦና መጠበቅ አለብን ምክንያቱም የተሳከ የዉድድር ዘመን ለማግኘት ይህ አስፈላጊ ነዉ ፤ ይህንን በቡድንህ ዉስጥ ትፈልገዋለህ። "

ስለ ሊንደሎፍ እና ማርሲያል

" ሊንደሎፍ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሰርቷል ፤ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆነ ነገ የምናየዉ ይሆናል ነገር ግን እሱ በአንድ የልምምድ ክፍለ ጊዜ ብቻ ነበር የነበረዉ ፤ ሁለት እና ሶስት ሳምንቶች አልፈዉት ነበር።
ማርሲያል ለነገዉ ጨዋታ ዝግጁ አይደለም። "

የአንቶኒ ዝዉዉር ለመጠናቀቀ እና የወረቀት ስራዎቹን ለማጠናቀቀ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ታዉቃለህ።

" አይ አላዉቅም "

እሱን [አንቶኒን] በሳምንቱ መጨረሻ በቡድንህ እንደሚኖር ተስፋ አለ??

" ተስፋ አድርጓለዉ ነገር ግን መጀመሪያ መጠናቀቀ አለበት "

ስለ ሌስተር ? የዉድድር አመቱን አሁን ባሉበት ሁኔታ መጀመራቸዉ እና የሊጉ መጨረሻ መሆናቸዉ ለብዙ ሰዎች አስገራሚ ይመስላል። ለጅማሯቸዉ ሀሙስ ዕለት ለሚያዘጋጁት ምላሽ እንዴት ጠንቃቃ መሆን ትፈልጋለህ?

" ያለፉት ሁለት ጨዋታቸዉን ተመልክቼ ነበር።በተጨማሪም በባለፈዉ የዉድድር አመት ምን ያህል ጥሩ እንደነበሩ እናዉቃለን። ይህንንም እስካሁን ባደረጉት ጨዋታ እንደተመለከትክ አስባለዉ። የጨዋታ ሀሳባቸዉ ለእይታ ጥሩ ነወ። እነሱ በጣም ጥሩ እግር ኳስን ይጫወታሉ ስለዚህ እዛ ዉጤት ለማግኘት በጣም ጥሩ መሆን አለብን። "

ኤሪክ የሰጡትን ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንን ይመስላል። ያቀረብኩላቹህ አንተነህ ነበርኩ
መልካም ምሽት

ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

@rossodiavolo
@man_united_ethio_fans
25.7K viewsAnte Z Reds, edited  18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:25:39 MATCH DAY PRESS CONFRENCE...

በ5ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የጨዋታ መርሀግብር ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ኪንግ ፓዉር ስታዲየም ተጉዞ ሌስተር ሲቲን የሚገጥም ይሆናል። አለቃ ኤሪክ ቴን ሀግም ከጨዋታው አስቀድሞ ጋዜጣዊ መግለጫን ሰጥተዋል።

ስለ አንቶኒ ያለዉ ሁኔታ እና አብረኸዉ እንደመስራትህ በእሱ ዉስጥ ያየዉ ነገር ምንድነዉ? በዩናይትድ ምን ስኬታማ ሊያደርገዉ ይችላል?

" መጀመሪያ እሱን ማስፈረም አለብን ፤ በክለቦቹ መካከል ስምምነት አለ ነገር ግን የወረቀት ስራዎች አልተጠናቀቁም ስለዚህ ስለ እዉነታዉ ብዙም በጥልቅ አልገባም። "

እሱ [አንቶኒ] አስፈላጊ ነው ብለህ የምታስበዉን ቦታ ይሞላል።

" ማጥቃት እና የማጥቃት ክፍሎች ላይ አሁንም ቡድኑን ማጠናከር አለብን ምክንያቱም ምንጨዋተዉ ብዙ ጨዋታ ነዉ ፤ ከአሁን ጀምሮ በሶስት ወይም በአራት ቀን ልዩነት ነዉ ምንጫወተዉ። እንደሚታወቀዉ የማጥቃት ስፍራ ተጨዋቾች ለድካም ቅርብ ናቸዉ ምክንያቱም ብዙ መሮጥ እና በከፍተኛ ስሜት መጫወት አለባቸዉ ፤ እኛም ይህንን በራሳችንን አጨዋወት ከእነሱ እንጠብቃለን። ስለዚህ እዛ ቦታ ላይ ቁጥሮችን እንፈልጋለን ነገር ግን ቁጥር ብቻ አይደለም ፤ ብዛት ብቻ አንፈልግም ጥራትም እንፈልጋለን። "

ማርቲን ዱብራቭካ ከዝዉዉሩ መጠናቀቅ በፊት ዩናይትድን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ዝዉዉር ከተጠናቀቀ ለዩናይትድ የመጨረሻዉ ዝውውር ነዉ ወይስ ሌላ ፊርማ ይኖራል?

" እንደምገምተዉ ከሆነ ለዚህ የዝውውር መስኮት የመጨረሻዉ ይሆናል ነገር ግን ትልቅ አጋጣሚ ካለ እንደ ትልቅ ክለብ ሁሌም ዝግጁ መሆን ይጠበቅብሀል። "

የአንቶኒ መምጣት ሮናልዶን የት ያደርገዋል? እሱ መጫወት እንደሚፈልግ ግልፅ ነዉ ፤ ይህ የእሱን የጨዋታ ጊዜ ይበልጥ ይቀንሰዋል? አሁንም የእቅዱ አካል ነዉ?

" ግልፅ ነዉ። እኔ የምለዉ እኛ ጥራት ያላቸዉን ተጨዋቾች እንፈልጋለን። ብዙ ጨዋታዎችን በወጥ አቋም ለመቀጠል ተጨማሪ ያስፈልገሀል። እኛም ለእዚህ ነዉ እየጣርን ያለነዉ። "

ዋን ቢሳካ አሁንም በእቅድ ዉስጥ ነዉ? በአያክስ የምታቀዉ ሰርጂኒዮ ዴስት ከባርሰሎና ይመጣል ስለሚባሉ ዜናዎችስ?

" ቢሳካ በእቅዴ ዉስጥ ነዉ ፤ በእዚህ ቡድን ዉስጥ ይቆያል። በዚህ ሲዝን በዚህ ቡድን የምንጫወት ይሆናል። "

ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

@rossodiavolo
@man_united_ethio_fans
25.2K viewsAnte Z Reds, edited  18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:25:26
24.6K viewsAnte Z Reds, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:05:58
እስከመቼ ለ 5 እና ለ 10 ሚሊዮን እያልን ተጫዋቾችን እናጣለን? ሌሎች ምንነቱ ላልታወቀ ተጫዋች 90 እና 100 እያወጡ አይደል እንዴ?

የሆኑ ክለብ ደጋፊዎች አሁን ላይ እያሰሙት የሚገኙት እሮሮ ነው! ሙድሪክን ይንሳኝ አንቶኒ ይችላል¡

@ezedin_iqbal
@man_united_ethio_fans
26.7K views𝙸𝙻𝙺𝙰𝚈 𝙴𝚉𝙴𝙳𝙸𝙽, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:54:01
HERE WE GO !

ጄምስ ጋርነር ወደ ኤቨርተን !

[Fabrizio Romano]

@ezedin_iqbal
@man_united_ethio_fans
27.9K views𝙸𝙻𝙺𝙰𝚈 𝙴𝚉𝙴𝙳𝙸𝙽, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:50:04
#Update

"አሁንም ማንችስተር ዩናይትዶች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት አንድ ሰው ማስፈረም ይችላሉ ብዬ አስባለሁ።"

"በእርግጥ ይህ ግምቴ ብቻ ነው። እባካችሁ ቃላቶቼን በቁም ነገር አትውሰዱ። አንዳንድ ምንጮች ለመናገር ነፃነት የሌለኝን ነገሮች ይነግሩኛል።"

"በእግር ኳስ ውስጥ ሁሉም ነገር በማንኛውም ሰዓት ሊለወጥ ይችላል።"

[Jonathan Shrager]

@ezedin_iqbal
@man_united_ethio_fans
27.8K views𝙸𝙻𝙺𝙰𝚈 𝙴𝚉𝙴𝙳𝙸𝙽, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ