Get Mystery Box with random crypto!

MATCH DAY PRESS CONFRENCE... በ5ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የጨዋታ መ | ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

MATCH DAY PRESS CONFRENCE...

በ5ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የጨዋታ መርሀግብር ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ኪንግ ፓዉር ስታዲየም ተጉዞ ሌስተር ሲቲን የሚገጥም ይሆናል። አለቃ ኤሪክ ቴን ሀግም ከጨዋታው አስቀድሞ ጋዜጣዊ መግለጫን ሰጥተዋል።

ስለ አንቶኒ ያለዉ ሁኔታ እና አብረኸዉ እንደመስራትህ በእሱ ዉስጥ ያየዉ ነገር ምንድነዉ? በዩናይትድ ምን ስኬታማ ሊያደርገዉ ይችላል?

" መጀመሪያ እሱን ማስፈረም አለብን ፤ በክለቦቹ መካከል ስምምነት አለ ነገር ግን የወረቀት ስራዎች አልተጠናቀቁም ስለዚህ ስለ እዉነታዉ ብዙም በጥልቅ አልገባም። "

እሱ [አንቶኒ] አስፈላጊ ነው ብለህ የምታስበዉን ቦታ ይሞላል።

" ማጥቃት እና የማጥቃት ክፍሎች ላይ አሁንም ቡድኑን ማጠናከር አለብን ምክንያቱም ምንጨዋተዉ ብዙ ጨዋታ ነዉ ፤ ከአሁን ጀምሮ በሶስት ወይም በአራት ቀን ልዩነት ነዉ ምንጫወተዉ። እንደሚታወቀዉ የማጥቃት ስፍራ ተጨዋቾች ለድካም ቅርብ ናቸዉ ምክንያቱም ብዙ መሮጥ እና በከፍተኛ ስሜት መጫወት አለባቸዉ ፤ እኛም ይህንን በራሳችንን አጨዋወት ከእነሱ እንጠብቃለን። ስለዚህ እዛ ቦታ ላይ ቁጥሮችን እንፈልጋለን ነገር ግን ቁጥር ብቻ አይደለም ፤ ብዛት ብቻ አንፈልግም ጥራትም እንፈልጋለን። "

ማርቲን ዱብራቭካ ከዝዉዉሩ መጠናቀቅ በፊት ዩናይትድን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ዝዉዉር ከተጠናቀቀ ለዩናይትድ የመጨረሻዉ ዝውውር ነዉ ወይስ ሌላ ፊርማ ይኖራል?

" እንደምገምተዉ ከሆነ ለዚህ የዝውውር መስኮት የመጨረሻዉ ይሆናል ነገር ግን ትልቅ አጋጣሚ ካለ እንደ ትልቅ ክለብ ሁሌም ዝግጁ መሆን ይጠበቅብሀል። "

የአንቶኒ መምጣት ሮናልዶን የት ያደርገዋል? እሱ መጫወት እንደሚፈልግ ግልፅ ነዉ ፤ ይህ የእሱን የጨዋታ ጊዜ ይበልጥ ይቀንሰዋል? አሁንም የእቅዱ አካል ነዉ?

" ግልፅ ነዉ። እኔ የምለዉ እኛ ጥራት ያላቸዉን ተጨዋቾች እንፈልጋለን። ብዙ ጨዋታዎችን በወጥ አቋም ለመቀጠል ተጨማሪ ያስፈልገሀል። እኛም ለእዚህ ነዉ እየጣርን ያለነዉ። "

ዋን ቢሳካ አሁንም በእቅድ ዉስጥ ነዉ? በአያክስ የምታቀዉ ሰርጂኒዮ ዴስት ከባርሰሎና ይመጣል ስለሚባሉ ዜናዎችስ?

" ቢሳካ በእቅዴ ዉስጥ ነዉ ፤ በእዚህ ቡድን ዉስጥ ይቆያል። በዚህ ሲዝን በዚህ ቡድን የምንጫወት ይሆናል። "

ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

@rossodiavolo
@man_united_ethio_fans