Get Mystery Box with random crypto!

[#የቀጠለ] በመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች የቡድኑ ከፍ ማለት በተመሳሳይ ተጨዋቾች ላይ ያሳደርከ | ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

[#የቀጠለ]

በመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች የቡድኑ ከፍ ማለት በተመሳሳይ ተጨዋቾች ላይ ያሳደርከዉ የሁኔታ ፣ የዝግጁነት ፣ የመነሳሳት ለዉጥ ነዉ ?

" ይህን እንደ ጅማሮ ነዉ ማየዉ ፤ አሁን ጥሩ መሰረት አለን ብዬ አስባለዉ ነገር ግን ይህ እኛ ማምጣት ከምንፈልገዉ ትንሹ ነዉ። ይህንን መነሳት በማየቴ ደስተኛ ነኝ እናም ይህንን መንፈስ እና የማሸነፍ ስነ ልቦና መጠበቅ አለብን ምክንያቱም የተሳከ የዉድድር ዘመን ለማግኘት ይህ አስፈላጊ ነዉ ፤ ይህንን በቡድንህ ዉስጥ ትፈልገዋለህ። "

ስለ ሊንደሎፍ እና ማርሲያል

" ሊንደሎፍ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሰርቷል ፤ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆነ ነገ የምናየዉ ይሆናል ነገር ግን እሱ በአንድ የልምምድ ክፍለ ጊዜ ብቻ ነበር የነበረዉ ፤ ሁለት እና ሶስት ሳምንቶች አልፈዉት ነበር።
ማርሲያል ለነገዉ ጨዋታ ዝግጁ አይደለም። "

የአንቶኒ ዝዉዉር ለመጠናቀቀ እና የወረቀት ስራዎቹን ለማጠናቀቀ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ታዉቃለህ።

" አይ አላዉቅም "

እሱን [አንቶኒን] በሳምንቱ መጨረሻ በቡድንህ እንደሚኖር ተስፋ አለ??

" ተስፋ አድርጓለዉ ነገር ግን መጀመሪያ መጠናቀቀ አለበት "

ስለ ሌስተር ? የዉድድር አመቱን አሁን ባሉበት ሁኔታ መጀመራቸዉ እና የሊጉ መጨረሻ መሆናቸዉ ለብዙ ሰዎች አስገራሚ ይመስላል። ለጅማሯቸዉ ሀሙስ ዕለት ለሚያዘጋጁት ምላሽ እንዴት ጠንቃቃ መሆን ትፈልጋለህ?

" ያለፉት ሁለት ጨዋታቸዉን ተመልክቼ ነበር።በተጨማሪም በባለፈዉ የዉድድር አመት ምን ያህል ጥሩ እንደነበሩ እናዉቃለን። ይህንንም እስካሁን ባደረጉት ጨዋታ እንደተመለከትክ አስባለዉ። የጨዋታ ሀሳባቸዉ ለእይታ ጥሩ ነወ። እነሱ በጣም ጥሩ እግር ኳስን ይጫወታሉ ስለዚህ እዛ ዉጤት ለማግኘት በጣም ጥሩ መሆን አለብን። "

ኤሪክ የሰጡትን ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንን ይመስላል። ያቀረብኩላቹህ አንተነህ ነበርኩ
መልካም ምሽት

ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

@rossodiavolo
@man_united_ethio_fans