Get Mystery Box with random crypto!

አስተኳሹ ዌንገር... ያንን የ90 ደቂቃ ፍልሚያ ምናልባትም ፈረንሳያዊዉ ሰው አርሴን ዌንገር ፈፅ | ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

አስተኳሹ ዌንገር...

ያንን የ90 ደቂቃ ፍልሚያ ምናልባትም ፈረንሳያዊዉ ሰው አርሴን ዌንገር ፈፅሞ ሊያስቡት አይፈልጉም ይሆናል... በፕሪሚየር ሊጉ ድንቅ ግስጋሴ ላይ የነበረውን አርሰናልን እና የክለቡን ጉምቱ በረኛ የዴቪድ ሴሞንን መረቦች አንድ ነጭ የ17 አመት እንቦቃቅላ ይደፍረዋል ብሎ ማን ጠበቀ...በዚህ እድሜኮ አንድ እንግሊዛዊ ቤቱ ቁጭ ብሎ ስለ ሳይንስ ፈተናው የሚያስብበት ወቅት ነው! ይህ ሰው ግን በዚህ እድሜው በ2002 የአርሰን ዌንገርን ጦር ድባቅ በመምታት ፊቱን ብሎም ረጃጅም ተምዘግዛጊ ቅልጥሞቹን ለአለም አስተዋወቀ።

ዌንገር የመቆጣት ስሜት ፊታቸው ላይ ይነበባል... ነገርግን በቅፅበት ስለ ነጩ ኮከብ አስተያየታቸውን በሚሰጡበት ወቅት ታዳጊው ላይ የሩቅ ተስፋ አብሪ ኮከብነት የሰነቀ ትንቢት ቢጤ ጣል አደረጉ!

" ይህ ልጅ ግሩም ነው! ወደፊት በትልቅ ደረጃም እንደማየው እርግጠኛ! ነኝ አሉ። ከዛ ጨዋታ በኋላ ነበር ዌንገር ሮኒን ለማስፈረም ያለመታከት መድከም የጀመሩት።

ግና የግልፍተኛው ወጣት አይን ለንደንን አልመረጠም... ሪፐብሊክ ኦፍ ማንቹሪያን የዋዛ ድንቅ ምርጫ ሆኖ ቀረ። ወትሮውኑ ግልፍተ አመል ያለባቸው ታዳጊዎች መልበሻ ቤት ከመበጥበጥ ባለፈ ታላቅ አንድምታ ከበስተጀርባቸው አለ ብለው የሚያምኑት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እየመረራቸውም ቢሆን ጣፋጩን ሮኒን ለማግኘት ወሰኑ...ከዴቪድ ቤካም እና ንጉሡ ካንቶና ተመሳሳይ መንገድ ትእግስታቸውን ቢፈታተናቸው እንኳን ወደፊት የሚያሳየው ትንታግ ሃይል ለቡድኔ ይጠቅማል በማለት ዋይን ሩኒን በዚህች ቀን አስፈርሙ...።

[ሚካኤል]

@Micky_united
@Man_united_ethio_fans