Get Mystery Box with random crypto!

Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ harunmedia — Harun Media - ሀሩን ሚዲያ H
የቴሌግራም ቻናል አርማ harunmedia — Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @harunmedia
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.42K

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-28 10:49:16
በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዬች ከፍተኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት የተመራ ልኡካን ቡድን በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዬች ድጋፍ አደረገ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 20/2015
...
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከከተማች ፣ከሀገራችን እና በወጭ ሀገር ከሚኖሩ ሙስሊሞች ያሰባሰበውን ከ5 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት ምግብ፣ አልባሳት፣የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፉን አድርጎል።
...
ድጋፉን ለማድረስ በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዬች ከፍተኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት ሼህ ፈትሁዲን ሀጂ ዘይኑ ሙቅና እና የስራ አስፈፃሚ አባልና የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሊድ መሀመድ ከነጃሺ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ ኸይር ፈላጊ የበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲሁም ተአውን የልማትና መረዳጃ እድር አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ደብረ ብርሃን ሲደርሱ ም/ከንቲባው ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
..
ልኡከካን ቡድኑ ሁለት መጠለያ ካምፖችን ከጎበኝ እና ድጋፉን ለማህበረሰቡ ካደረሰ በኃላ ከደብረ ብርሃን ከተማው እስልምና ጉዳዬች ጋር ምክክር በማድረግ ጉዳዩ በቀጣይ መጪው ግዜ ክረምት ከመሆኑ አንጻር እንዲሁም የቲም ህፃናት በስፍራው ስለሚገኙ ትኩረት ተሰጥቶ በጋራ የማህበረሰባችንን ችግር ለማቀለል በቀጣይነት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
2.3K views07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 19:12:33
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት  ከዘጠኝ ባንኮች ጋር ስምምነት አደረገ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዚያ 18/15
...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ የ2015(1444) የሀጅ መስተንግዶውን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመፈጸም ምክር ቤቱ ከዘጠኝ ባንኮች ጋር የውል  ሰምምነት አድርጓል።

ጠቅላይ  ምክር ቤት   ውል የፈጸመባቸው ባንኮች፦

1.ዘምዘም ባንክ
2.ሂጅራ ባንክ
3.ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
4.ኦሮምያ ህብረት ሥራ ባንክ
5.ዳሽን ባንክ
6.ኦሮምያ ባንክ
7..አዋሽ ባንክ
8.አቢሲንያ ባንክ
9.ወጋገን ባንክ  ሲሆኑ ሁጃጆች ጠቅላይ  ምክር ቤቱ ከየትኛውም ባንክ የተለየ ስምምነት ያላደረገ መሆኑን ተገንዝበው  በተመሳሳይ  ዉል ከፈጸመባቸዉ  በአቅራቢያቸው  ከሚገኙት ባንኮች ግልጋሎት ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.6K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 11:17:56
የኢድ ሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሀይል አስታወቀ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 13/2015
...
የ1ሺህ 444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት ስነ ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
...
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አልፈጥር በዓል የሶላት ስነ ስርዓት በርካታ ህዝበ ሙስሊም በተገኘበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ተካሂዷል።
...
ከንጋት ጀምሮም ወደ ሶላቱ ቦታ በሚደረግ ጉዞም ሆነ የሶላት ስነስርአቱ በሚካሄድበት ወቅት አንዳችም በዓሉን የሚያውክ ሁኔታ እንዳይፈጠርና የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም የፀጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣታቸው ተመላክቷል።
...
በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት እንደነበረው የማስተባበሩን ሚና በመወጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ነው የተገለፀው።
..
በዚህም የአዲስ አበባ ነዋሪን ጨምሮ የሶላት ስነ ስርአቱ በሚካሄድበት ስፍራ በመገኘት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል ምስጋና አቅርቧል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
2.0K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 11:17:45
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለመስገጃ የሚሆን 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሰጠቱን ዛሬ አስታውቋል።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 13/2015
...
የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ዛሬ የኢድ አልፈጥር በዓል በባህር ዳር ስታዲየም በሚከበርበት ወቅት ነው ይህንን ዜና ማብሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
..
ዶ/ር ድረስ ሳህሉ እንደተናገሩት "ለብዙ ጊዜ ስትጠይቁት የነበረ የመስገጃ ቦታ አሁን በክልልም ፀድቆ የመጣ ስለሆነ ምናልባትም በሚቀጥለው ዓመት በደንብ ሰርታችሁት እዚህ ሳይሆን እዛው ከተፈቀደላችሁ ቦታ ላይ የምታከብሩት ይሆናል። ክልሉ ያቀረባችሁትን ጥያቄ እኛ አፅድቀን ልከን ክልሉም ተቀብሎት 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የኢድ አልፈጥር በዓል የምናከብርበት ቦታ ተፈቅዷል። " ብለዋል።
...
ከንቲባው ይህንን ንግግራቸውን ሲያደርጉ የባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ምእመን እጅግ በደስታ ስሜት ተክቢራውን አሰምቷል።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.9K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 17:33:07
የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ-አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር በረመዳን ወቅት የነበረውን የመረዳዳትና የአብሮነት እሴቱን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስታወቀ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 12/2015
...
የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1444ኛው የኢድ-አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በወራቤ ከተማ በሚገኘው ጊዜያዊ ጽህፈት ቤት አስተላልፏል፡፡
...
የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሀጂ ሙሃመድ ከሊል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1444ኛው አመተል ሂጅራ ጾም ፍች የእንኳን አደረሳችሁ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
...
ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ውስጥ በርካታ በጎ ተግባራትና ከፈጣሪያቸው ጋር የሚያቀራርቡቸውን የአምልኮ ስርዓቶች በከፍተኛ መነሳሳት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው ይህንን በጎ ተግባር ከረመዳን ፆም በኋላም አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
...
የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጸሃፊ ሼህ ኡስታዝ ሳዲቅ ወጌቦ በበኩላቸው ህዝበ ሙስሊሙ ጾም ማገባደጃ ላይ እንዲያወጣ ግዴታ የሆነበትን ዘካቱል ፈጥር በግዜው እና በአግባቡ ማውጣት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
3.2K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 20:29:32
ለደሴ ከተማ
...
1444ኛው የረመዷን ወር የዘካተል ፊጥር የሚወጣ አይነትና የዋጋ ተመንን በተመለከተ የደሴ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እንደሚከተለው አሳውቋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.4K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 19:34:37
አማራ ባንክ ከኢማን ኢስላማዊ ማህበር ጋር በመተባበር በደብረ ብርሃን ለተፈናቀሉ ወገኖች የአስቤዛ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 11/2015
...
ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ አግኝቶ በቅርቡ ስራ የጀመረው አማራ ባንክ ከኢማን ኢስላማዊ ማህበር ጋር በመተባበር በደብረ ብርሃን ለተፈናቀሉ ወገኖች የአስቤዛ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። ባንኩ በማኅበራዊ ድጋፍ መስክ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ከማኅበራዊ ሚዲያ መገኛዎቹ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
..
አማራ ባንክ
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.5K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 19:51:22
በሀላባ ዞን መቀመጫ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በዛሬው እለት ደማቅ የኢፍጣር ፕሮግራም ተካሔደ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 9/2015
...
በሀላባ ዞን መቀመጫ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በዛሬው እለት ደማቅ የኢፍጣር ፕሮግራም ተካሔደ። ለሶስተኛ አመት በተካሔደው በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ የከተማው ነዋሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተውበታል።
...
ሀሩን ሚዲያ
1.9K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 19:44:22
በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው መቀሌ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተከናወነ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 9/2015
..
በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው መቀሌ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተከናወነ። በዛሬው እለት በተከናወነው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የክልሉ መጅሊስ አመራሮች እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ታድመዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
1.8K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 15:35:08
የውጪ ኦዲት ምርመራን ግኝት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዚያ 8/2015
...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምክር ቤቱን የፋይናንስ አሰራርን ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

ከነዚህም ውስጥ ፦
1ኛ. በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤትን ከጥር 1/2012 እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ል የሁለት አመት ከሰባት ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴን እንዲሁም

2ኛ. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱን ከታህሳስ 1/2012 እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ል የሁለት አመት ከስምንት ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴን በሰርቲፋይድ ቻርተርድ አካውንታንት በሆኑና ሕጋዊ የሙያ ፍቃድ ባላቸው በውጪ አዲት የፋይናንስ እንቅስቃሴያቸውን ለማስመርመር ግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ባወጣው መሠረት የኦዲት ምርመራ ስራቸውን በማጠናቀቅ የኦዲት ግኝት ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም በውጪ የኦዲት ተቋሙ የኦዲት ምርመራው ግኝት ሪፖርተርን መሠረት በቀጣይ ተጠያቂነት መሠረት ባደረገ መልኩ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የወጪ የኦዲት ተቋሙ የፋይናንስ ግኝት ምርመራ መሠረት በማድረግ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚወሰዱ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
2.0K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ