2023-01-28 19:45:41
በኮልፌ ቀራንዮ የእሳት ቃጠሎ አደጋ የደረሰበትን መስጂድ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጉበኙ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 20/2015
...
በኮልፌ ቀራንዮ ክፈለ ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ አባ ጃሌ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ባልታወቀ ምክኒያት መስጂድ ተቃጥሏል። ይህንኑ ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፃሃፊ ሼህ ሁሴን በሽር ቃጠሎው ወደ ተከሰተበት ስፍራ አቅንተው ጉብኝት አድርገዋል።
...
በጉብኝታቸው ወቅት የከተማው ጠቅላይ ምክር ቤት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አፋጣኝ የመልሶ ግንባት ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል። የቃጠሎ ምክኒያት ለጊዜው ምን እንደሆነ ባይታወቅም ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ በመሆን የማጣራቱ ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
...
ቃጠሎው ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰአት ገደማ መድረሱን የገለፁት የወረዳው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ አህመድ መሀመድ እኛ እንደ አካባቢ ማህበረሰብ የሚጠበቅብንን ሁሉ አድርገን መስጂዱን ወደ ነበረበት ለመመለስ እንጥራለን፣ በተጨማሪም በተሻለ መልኩ ለመገንባት ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግልን ሲል ጥሪ አቅርበዋል።
..
ፖሊስ አካባቢው ላይ ተገኝቶ ጥብቃ እያደረገ ሲሆን እሳቱ በተነሳበት ወቅት የኮልፌ ቀራንዮ ክፈለ ከተማ እሳትና አደጋ ሰራ አመራር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ቃጠሎው ወደ አጎራባች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ በማድረግ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጓል። የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አደጋውን ለመቆጣጠር ርብርብ ያደረጉ አካላትን በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
...
መረጃው የአ/እስ/ጉ/ከ/ም/ቤት ነው።
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራ
ም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
3.5K views16:45