2022-07-15 18:21:29
የፍትህ ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጋር በመተባበር ጎንደር፣ ወራቤና ጂንካ አካባቢ የተፈጸሙ ወንጀልችን ምርመራ አድርጌያለሁ ሲል ይፋ አድርጓል።
..
ሀሩን ሚዲያ፥ ሐምሌ 8/2014
..
የፍትህ ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጋር በመተባበር ጎንደር፣ ወራቤና ጂንካ አካባቢ የተፈጸሙ ወንጀልችን ምርመራ አድርጌያለሁ ሲል ይፋ አድርጓል። በፍትህ ሚንስቴር የጠቅላይ አቃቤ ህግ ሕግ ዘርፍ ሚንስቴር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ እና በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ኦፕሬሽን መምሪያ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙልኢሳ አብዱሳ በጋራ በመሆን ነው መግለጫውን የሰጡት
..
በመግለጫቸው በጎንደር ሙስሊሞች፣ የሙስሊም ንብረቶችና መስጅዶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት "ግጭት" በሚል ቃል የገለጹት ሲሆን መነሻውም ተራ የድንጋይ ጠብ ነው ሲሉ ደምድውታል። ከግጭቱ በፊት የነበሩ የጥላቻ ቅስቀሳዎችና የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሊደረግ በመታሰቡ ሳቢያ የነበረውን የጥቃት ሒደት በሙሉ እንዳልነበረ በሚመስል መልኩ ሪፖርቱ ላይ ያልተካተተ ሲሆን የግጭቱ ምክንያት ድንጋይ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
..
በተቃራኒው በወራቤ የነበረውን ክስተት ግን "ግጭት" በሚል ከመጥራት ይልቅ በተቀናበረ መልኩ የተካሔደ ጉዳት ማድረስ አድርገው አቅርበውታል። ጉዳት አድራሾችንም ከጎንደሩ ጥቃት አድራሻች በተለየ መልኩ "ጽንፈኛ ሀይሎች" ሲሉ ገልጸዋቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሀይማኖት መምህራን ሳይቀር ቅስቀሳ ተደርጓል በሚልም ተነግሯል። ሪፖርት አቅራቢው ሚንስቴር ዴኤታም ስለቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ሲገልጹ ስሜታዊ ሁነው ታይተዋል።
..
በጎንደር በተፈጸመው ጥቃት ሳቢያ የጎንደር ሙስሊም ከተማው እየለቀቀ የሚገኝ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ድረስ ደህንነታቸው አደጋ ላይ በመሆኑ ሳቢያ ከቀናት በፊት የተከበረው የኢድ አል አድሀ በአልም ቤታቸው እንዲያሳልፉ የዞኑ መጅሊስ መግለጹ ይታወሳል።
..
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
4.5K views15:21