2022-07-16 15:56:29
የፌዴራል አቃቤ ህግና የፌዴራል ፖሊስ በጥምረት አጣርተነዋል ባሉት የጎንደሩ ጥቃት ዙሪያ የሚከተለውን ድምዳሜ አቅርበዋል፦
..
❝ግጭቱ ባህሪው ቀድሞ ታስቦበት ያልነበረ በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ የተፈጠረ ነገር ግን የሰፋ፤ የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን የማምለኪያ ቦታ እና የንግድ እንዲሁም የመኖሪያ ቤቶችን በመምረጥ ጉዳት በማድረስ፤ የእስልምና ዕምነት ተከታዮችም ደግሞ በአጸፋው የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች የንግድ ቦታ ላይ ጉዳት አድርሰዋል❞
..
ይህንን በተመለከተ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንደ ሚዲያ ለታሪክ ይሆን ዘንድ እንጠይቃለን፦
..
1/ የጎንደር ከተማ እስልምና ጉዳዩች ም/ቤት በጎንደር የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ባዘጋጀው ሪፖርት ገጽ 2 ጀምሮ ጥቃቱ በአንድ ጀንበር በድንገት የተፈጠረ ሳይሆን በተለይም ከ2010 ጀምሮ ዘመቻ ሲደረግበት የነበረ እንደሆነ በመዘርዘር ስጋቶችን ለሚመለከተው አካል ጭምር በተደጋጋሚ ሪፖርት ማድረጉን ገልጿል። በዚህ መልኩ የነበረውን ስጋት ሁሉ ችላ ባለ መልኩ ጥምር መርማሪ ቡድኑ "ቀድሞ የታሰበበት አልነበረም" ሲል የመረጃና የምርመራ ምንጩ ምንን መሠረት ያደረገ ነበር? የአካባቢውን ሙስሊምና የከተማውን ወይንም የዞኑን መጅሊስ ሀሳብና ማስረጃዎች እንዴት ሳያካትትና ምርመራ ሳያደርግ ሊደመድም ቻለ?
..
2/ ጥቃቱ ከመፈጸሙ ከአንድ አመት ጀምሮ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በኩል የማኅበረ ቅዱሳን መዋቅሮች "የጎንደር ከተማ በሙስሊሞች ተወረረ" የሚል አደገኛ ስልጠናዎችን ለአብነት ተማሪዎችና ለዩንቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ሲሰጡ እንደነበር በዚህ ሚዲያ ሳይቀር የተገለጸ ሲሆን የስልጠና ማንዋል ፓወር ፖይንቱም ሳይቀር እጃችን ገብቶ በተከታታይ ፕሮግራም የሰራንበት ጉዳይ ነበር። ከሁለት አመት በፊት በሚዲያችን የተሰራውን ፕሮግራም በዚህ ሊንክ መከታተል ይቻላል፦
ይህ ስልጠና በባለቤቶቹ ሳይቀር የሚታወቅና ማስተባበያ እንኳን ያልተሰጠበት ሁኖ ሳለ ጥምር መርማሪ ቡድኑ ግን ምንም ጥቃቱን ሊፈጥር የሚችል ሞቲቭ ከዚያ በፊት እንዳልነበረ ሲገልጽ እነዚህን መረጃዎች ሳይደርሱት ቀርተው ነው ወይንስ ምክንያቱ ምንድን ነው?
..
3/ በማኅበራዊ ሚዲያ በማስተማር የሚታወቁና በጎንደር የሚኖሩ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሳይቀር እጅግ አደገኛ መልዕክት ያለምንም ሀፍረት በማኅበራዊ ሚዲያ ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ይታወሳል። ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል የሆነው መምህር ዮርዳኖስ የተባለ በጎንደር የሚኖር ግለሰብ በግልጽ "ጉልበታችንን አንድ ቀን ታዩታላችሁ" የሚል መልዕክት ሳይቀር ሲያስተላልፍ እንደነበር ይታወሳል። የግለሰቡን ንግግር በዚህ ሊንክ ያገኙታል፦
https://t.me/harunmedia/655
መሠል ቅስቀሳዎች በከተማዋ በስፋት ሲሰራጩ እንደነበር በተደጋጋሚ የተገለጸ ሲሆን በጥምር መርማሪ ቡድኑ ሪፖርት ውስጥ ግን ምንም ነገር እንዳልነበር እንዴት ሊገለጽ ቻለ?
..
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
5.0K views12:56