2023-04-08 20:04:14
ታላቁ ኢፍጣር በኢትዮጵያ ሦስተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ-ግብር በዛሬው እለት ተካሔደ ተካሄደ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ መጋቢት 30/2015
...
ታላቁ ኢፍጣር በኢትዮጵያ ሦስተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ-ግብር "ኢፍጣራችን ለወገናችን" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ተካሂዷል። መርሐ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፉ፣ የዛሬው መርሐ-ግብር በጦርነት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ድጋፍ የምናሰባስብበት በመሆኑ ደስታችንን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ብለዋል።
...
ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በበኩላቸው፣ በሀገር ደረጃ ለሦስተኛ ጊዜ የተካሄደው መርሐ-ግብሩ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸው፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንድነቱን እና ሀገራዊ አብሮነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚጠቅምም ተናግረዋል። በመርሐ-ግብሩ በቁርዓን መቅራት ኢትዮጵያን ወክሎ በዱባይ በተዘጋጀው በ26ኛው ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር ላይ በሁለተኛ ደረጃ ውድድሩን ላጠናቀቀው ቃሪዕ አባስ ሐዲ የዕውቅና ሰርተፊኬት ተብርክቶለታል።
...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ “ልጃችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በቁርዓን መቅራት 2ኛ ደረጃን ይዞ ስማችንን ከፍ በማድረጉ ለኢትዮጵያ በተለይም ለሙስሊሞች ኩራት እና ደስታን ፈጥሮልናል” ሲሉ ቃሪዕ አባስ ሐዲን አወድሰዋል። በመርሐ-ግብሩ ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የተወጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.7K views17:04