2023-03-05 16:38:05
በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ የሚገነባው የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከልና አዳሪ ት/ቤት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በዛሬው እለት በመካሔድ ላይ ይገኛል
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 26/2015
...
በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ የሚገነባው የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከልና አዳሪ ት/ቤት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በዛሬው እለት በመካሔድ ላይ ይገኛል። ከአዲስ አበባ 700ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የደቡብ ኦሞዋ መናገሻ ጂንካ ከተማ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ፣ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ፣ የዞኑ መስተዳድርና የከተማው ከንቲባ በተገኙበት የተቋሙ መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
...
ተቋሙ ግንባታው ሲጠናቀቅ መስጂድ፣ የሂፍዝ ማዕከል፣ ከ1-12ኛ ክፍል አዳሪ ትምህርት ቤትና ሌሎች ሁለንተናዊ አገልገሎቶችን እንዲሰጥ ታቅዶ በ 10,000 ካ.ሜ ላይ የሚያርፍ እንደሚሆን ተገልጿል። ጂንካ ከተማ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች መናገሻ ከተማ በዋናነትም የ16 ነባር ብሄረሰቦች መገኛ ስትሆን ብዙም የእስልምና ብርሃን ያልፈነጠቀበት አካባቢ ነው።
...
በገቢ ማሰባሰቢያ መርኅ ግብሩ ላይ የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ፣ ሸይኽ ሱልጣን አማን፣ ሸይኽ መሀመድ ሃሚዲን፣ ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ዑለሞችና ዱዓቶች ተገኝተዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.6K views13:38