Get Mystery Box with random crypto!

የእለቱ አበይት ኢስላማዊ መረጃዎች .. ➭ የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የእለቱ አበይት ኢስላማዊ መረጃዎች
..
➭ የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ኢስላማዊ ማዕከል እና አዳሪ ትምህርት ቤት ለመስራት የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል።
...
➭ በገርባ ከተማ በሀጅ ሙሀመድ ራፊዕ ስም የተሰየመዉ ሁሉን አቀፍ መድረሳና ኮሌጅ አስመልክቶ በዛሬው እለት ሰፊ የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሒዷል።
...
➭ ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የምገባና የአረጋዊያን መጠለያ ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
...
➭ በአፋር ክልል መናገሻ ሰመራ ከተማ በዛሬው እለት ደማቅ የሆነ የዳዕዋ ፕሮግራም ተካሒዷል።
...
➭ በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው መቱ ከተማ በዛሬው እለት ታላቅ የዳዕዋና እና የዱዓ ፕሮግራም ተካሒዷል።
...
➭ ነሲሓ ኮንፈረንስ በጅማ ከተማ በታላቅ ድምቀት በዛሬው እለት ተካሒዷል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j