2023-03-19 13:32:11
ዱዓቶች ተቀናጅተው ማህበረሰቡን እንዲያስተምሩ ተጠየቀ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ መጋቢት 9/15
..
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዳዕዋ ስራን የተቀናጀ ለማድረግ ከዱዓቶች ጋር የትውውቅና የምክክር መድረክ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሠብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ። በምክክር መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ዑለማዎች የነብያት ወራሾች በመሆናቸው ዑማውን ዕለት ከዕለት በተቀናጀ መልኩ የማስተማር ኃላፊነት እንዳለባቸው አስታውሰው እስካሁን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ምንዳውን ከአሏህ ብቻ በመፈለግ ሕብረተሰባችንን በማስተማራችሁ በዚህችኛዋ አለም ስኬት በዛችኛዋ አለም ደግሞ ጀነትን እንዲወፍቃቸው ምኞታቸውን ገልፀዋል።
...
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ማጠናቀቂያ ላይ አንደተናገሩት "ከቀናት በኋላ ትልቅ ዕንግዳን እንቀበላለን ለዚህ ለተከበረው ወር በመድረሳችንን ፈጣሪያችንን አሏህ ሰ.ወ እናመሠግናለን " ብለዋል። ሁላችንም ሰዎች በመሆናችንን መሳሳታችን የማይቀር በመሆኑ በስራ ሂደት የተቀየማችሁኝ "እኔን አውፍ እንድትሉኝ። ዑማውም አውፍ እንዲለኝ መልዕክት አስተላልፉልኝ" ብለዋል
...
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አባል ሼይኽ አሚን ኢብሮ የዳዕዋ ስራ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የጀርባ አጥንት ስራ በመሆኑ ዱዓቶች በመቀናጀት ዑማውን ከመቼውም በተሻለ መልኩ ዲናዊ ትምህርት መስጠት ይገባል ብለዋል። በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው በተደረገው የትውውቅና የምክክር መድረክ ላይ በዶክተር ጀይላን ኸድርና በዶክተር ሙሐመድ ሐሚዲን ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
...
ይህ መሰሉ የምክክር መድረክ በጠቅላይ ምክር ቤቱ መደረጉን የውውይቱ ተሳታፊ የሆኑት ዱዓቶች አመስግነው በቀጣይ መሰል ውይይቶች በስፋት መቀጠል እንደሚኖርበት አሳስበዋል። በምክክር መድረኩ ላይ ከክልልና ከተማ አስተዳደር የመጡ ታዋቂ ዱዓቶች ተገኝተውበታል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.7K views10:32