Get Mystery Box with random crypto!

Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ harunmedia — Harun Media - ሀሩን ሚዲያ H
የቴሌግራም ቻናል አርማ harunmedia — Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @harunmedia
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.42K

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-17 19:26:19
1.4K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 21:34:17
የፌዴራል መጅሊሱ ልዑካን ቡድን አባላት የደቡብ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሀድያ ጥቃት ዙሪያ ውይይት አደረጉ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 8/2015
...
የፌዴራል መጅሊሱ ልዑካን ቡድን አባላት የደቡብ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሀድያ ጥቃት ዙሪያ ውይይት አደረጉ። በውይይታቸው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመልካም አስተዳደር ዳይሬስክቶሬት ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ አብርሀም አለሙ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከዛም በተጨማሪ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተመስገን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
...
በውይይቱ ከተነሱ ቁልፍ ነጥቦች መካከል በዞኑ ተፈጥሮ የነበረውን ጥቃት በዝርዝር ያሳወቁ ሲሆን ያለውን ችግር በክልል ደረጃ ልዑካን ቡድን ተቋቁሞ እንደሚፈታም መግባባት ላይ ተደርሷል። የተነገራቸው መረጃ "ግጭት" የሚል እንደነበረ ገልጸው ጉዳዩን ግን ቦታው ድረስ መጣራት የሚያስፈልገው መሆኑን መተማመን ላይ ደርሰዋል። ኮሚቴው በቀጣይ ጉዳት የደረሰበትን ጭንጎ ወረዳ እንደሚጎበኙ ለሀሩን ሚዲያ ገልጸውልናል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
877 views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 19:54:43
የፌዴራል መጅሊስ ልዑካን ቡድን በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል ተገኝተው ተጎጂዎችን ጎበኙ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 7/2015
...
የፌዴራል መጅሊስ ልዑካን ቡድን በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል ተገኝተው ተጎጂዎችን ጎበኙ። በጉብኝቱ ወቅት ጽንፈኛ የአክፍሮተ ሀይል አካላት ያደረሱትን ጉዳት ከጎጂዎቹ አንደበት የሰሙ ሲሆን የተጎጂዎችን ሙሉ ወጭ መጅሊሱ በመሸፈን እንደሚያሳክምም ቃል ገብተዋል።
...
ከዚህም በተጨማሪ ጉዳዩን ከክልል እስከ ቀበሌ ዘንድ ጭምር በመሄድ እንደሚከታተሉና አጥፊዎቹ ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት እንዲያገኙ ግፊት እንደሚያደርጉ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸውላቸዋል። የጉዳት መጠኑን ለማጥናትም በሆስፒታሉ የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች ጋር ስብሰባ በማድረግ መረጃዎችን ያዋቀሩ ሲሆን ተጎጂዎችን በተመለከተ የሚመለከተው የመንግስት አካል መጥቶ ያሉበትን ሁኔታ አለማየቱን አረጋግጠዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
2.0K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 16:07:53
በኡስታዝ አብዱልመጂድ ሁሴን (ረሂመላህ) አስተባባሪነት ተጀምሮ የነበረው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ድሃ ወዲህ መስጂደል አንዋር ግንባታ ማስጨረሻ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 7/2015
...
በኡስታዝ አብዱልመጂድ ሁሴን (ረሂመላህ) አስተባባሪነት ተጀምሮ የነበረው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ድሃ ወዲህ መስጂደል አንዋር ግንባታ ማስጨረሻ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።
...
በፕሮግራሙ ላይ ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ ፣ ኡስታዝ ሙሀመድ አባተ የሰሜን ወሎ ዞን እና ወልዲያ ከተማ አዲሱ የመጅሊስ አመራሮች ፣ሀጂ ያሲን እና ሀጂ ሲራጅ እንዲሁም የወልዲያ ከተማ ህዝበ ሙስሊም ተገኝተዋል። ግንባታው በኮሮና እና በጦርነት ምክንያት የተስተጓጎለ ሲሆን የመስጂዱ ኪሚቴና የአካባቢው ተወላጆች ግንባታውን ለማስጨረስ ጥረት ጀምረዋል። የዚህ አጅር ተካፋይ መሆን ለሚፈልጉ በሚከተሉት አካውንቶች ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል።
...
ንግድ ባንክ - 1000518796554
አዋሽ ባንክ - 013201077043800
ዘምዘም ባንክ - 0019647420101
ኦሮምያ ባንክ - 1547136200001
...
ሙሉ መሰናዶውን ሀሩን ሚዲያ ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል።
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራ፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
818 views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 10:29:36
❝...በመኖሪያ ቤታችሁም ቢሆን ማምለክ አትችሉም..❞

የሀድያ ሙስሊሞች ከደረሰባቸው ግፍ ውስጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ከተናገሩት፦
...


1.7K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 18:38:11
በዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃን የተመራ የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ የታላቁ አንዋር መስጂድን አሁናዊ ሁኔታን ጎበኙ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 5/2015
...
በዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃን የተመራ የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ከኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ከሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ጋር በመሆን የታላቁ አንዋር መስጂድ አሁናዊ ሁኔታን ጎብኝተዋል። የታላቁ አንዋር መስጂድና ኻጢብ በሆኑት በሼኽ ጧሐ ሙሐመድ ሀሩንም የታላቁ አንዋር መስጂድን ታሪክና አሁናዊ ሁኔታን ለልዑኩ ገለፃ አድርገዋል።
...
ልዑኩ በታላቁ አንዋር መስጂድ በመገኘት መስጂዱን የጎበኙ ሲሆን የጁምዓ ሰላትም ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመሆን በጋራ ሰግደዋል። ዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃንም በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላት ከጀምዓው ጋር የመስገድ እድል ስላገኙ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። የአለም አቀፍ ሙስሊሞች ሊግ ልዑካን በኢትዮጵያ የጀመሩትን የስራ ጉብኘት በሌላ መርሃ ግብርም የሚቀጥሉ ይሆናል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.5K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 21:45:17
የሀዲያ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በዞኑ የተፈጸመውን ድርጊት በማስመልከት አጥፊዎች ለህግ ቀርበው ውሳኔ እንዲያገኙ ጠየቀ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 4/2015
..
የሀዲያ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በዞኑ የተፈጸመውን ድርጊት በማስመልከት አጥፊዎች ለህግ ቀርበው ውሳኔ እንዲያገኙ ጠይቋል። በሀድያ ዞን በአንሌሞ ወረዳ በጪንጎ ቀበሌ በባለፈው የገና በአል ከተለያዩ ቦታዎች የተውጣጡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነን የሚሉ አካላት በመስጅድና በሙስሊሙ መኖሪያ ቤት በመግባት ጥቃት መፈጸማቸውን የገለጸው መግለጫው ሰዎችን በግድ ሀይማኖታቸውን እንዲቀይሩ በማለት ከ30 በላይ ሰው ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን በዝርዝር ያትታል።
...
አጥፊዎቹ ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳዩ በህግ ሒደት እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን ይህንን ጉዳይ የሚከታተሉ ኮሚቴዎች መዋቀራቸውንም አያይዞ ገልጿል። ከተጎጂዎች የሞተ ሰው አለመኖሩ የተገለጸ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ግን በወራቤ ኮ/እ ሆስፒታል በተገቢው ሁኔታ እየተከታተሉ መሆናቸውን አሳውቋል። የደቡብ ክልል መጅሊስ እና የፌደራል መጅሊስ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቋል።
..
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራ፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.7K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 15:17:16
2.0K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 15:17:11
ሀሩን ሚዲያ በሀድያ ዞን በመገኘት ከሰሞኑ በሙስሊሞች ላይ የተደረገውን ጥቃት በማስመልከት ተጎጂዎችን አነጋገረ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 3/2015
...
➭ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል በመገኘትም ጉዳት የደረሰባቸውን ሙስሊሞች አናግሯል
...
ሀሩን ሚዲያ በሀድያ ዞን በመገኘት ከሰሞኑ በሙስሊሞች ላይ የተደረገውን ጥቃት በማስመልከት ተጎጂዎችን አነጋገረ። ጽንፈኛ በሆኑ የአክፍሮተ ሀይላት አማካኝነት በገዛ ቀያቸው ድብደባና እንግልት የደረሰባቸው ሙስሊሞች አሁን ላይ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ዘገባ ሰርቷል። በአሁኑ ሰአት 30 የሚጠጉ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን 7ቱ የከፋ ጉዳት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
...
የሀድያ ዞን ሙስሊሞችን በትምህርት ቤት ህግጋት ዙሪያ ጫና ከመፍጠር ጀምሮ እስከ መሠረታዊ የአኗኗር ህይወታቸው ላይ እምነታቸውን መሠረት ያደረገ ከፍተኛ በደል ሲደርስባቸው መቆየቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል። ከሰሞኑ የገና በአልን አስታከው አካባቢው ላይ የተቀናጀ ጥቃት በመክፈት ጉዳት ያደረሱት እነዚህ አካላት በዋናነት የዞኑን አስተዳደር የተመኩ ግለሰቦች እንደሆኑ ጨምረው ገልጸውልናል። በዚህ ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ጽንፈኛ ግለሰቦች እስከአሁን ድረስ ለህግ ያልቀረቡ ሲሆን ነዋሪዎች በዞኑ ለመኖር በእምነታቸው ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ገልጸዋል። የሚመለከተው የህግ አካል እንዲሁም መጅሊሱ ያሉበትን ሁኔታ ተረድቶ በቂ ትኩረት እንዲሰጣቸውም ተማጽነዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ ከተጎጂ የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ያደረገውን ቆይታ በአሏህ (ሱ.ወ) ፍቃድ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
..
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራ፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
2.1K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 19:56:27
የአለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ከሶስት አስርተ አመት በኋላ አወሊያን ጎበኘ
..
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 2/2015
...
ከሰባ ሀገራት በላይ በትምህርት በጤና እና በልማት የበጎ አገልግሎት ስራው የሚታወቀው አለም አቀፉ የሙስሊሞች ሊግ ከሶስት አስርት አመት በኃላ የአወሊያን አሁናዊ ሁኔታን በልዑኩ አማካኝነት በተቋሙ በመገኘት ጉብኝት አካሂዷል።
...
ልዑኩ በሊጉ የአውሮፖ እና በአሜሪካ ዋና ዳሬክተርና የኢስላሚክ ሊግ የዋና ፀሐፊዉ አማካሪ በሆኑት በዶክተር አብዱል አዚዝ ሰርሃን የተመራ ሲሆን ሊጉ ለአስርት አመታት ሲያስተዳድር የነበረውን አወሊያን ለአለም አቀፉ ኢስላማዊ ዕርዳታ ድርጅት አስረክቦ ከሀገር ከወጣ ከ ሶስት አስር አመት በኃላ በልዑካን ደረጃ ሲጎበኝ ይህ የመጀመሪያው ነው።
...
የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ጀማል መሐመድ እና የአወሊያ ስራ አስኪያጅ በሆኑት ሀጂ ሰዒድ አስማረ አማካኝነት የአወሊያን አሁናዊ ሁኔታን ለልዑኩ ገለፃ ተደርጎላቸዋል። የአለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ የዋና ፀሐፊዉ አማካሪና የልዑካኑ መሪ ዶክተር አብዱላዚዝ ሰርሃን በአወሊያ ማህበረሰብ የተደረገላቸውን ልዩ የሆነ አቀባበል መደሠታቸውን ገልፀው በቀጣይ ከአወሊያ ጋር አብሮ ለመስራት ከሚመለከተው አካል ጋር ዉይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል። ዛሬ በተደረገው የልዑኩ ጉብኝት ላይ የአወሊያ መስጂድ ኢማም የሆኑት ሼህ ዑመር መሐመድ ወሌን ጨምሮ የአወሊያ የማህበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራ፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.6K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ