Get Mystery Box with random crypto!

በዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃን የተመራ የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ የታላቁ አንዋር መስጂድን | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

በዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃን የተመራ የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ የታላቁ አንዋር መስጂድን አሁናዊ ሁኔታን ጎበኙ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 5/2015
...
በዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃን የተመራ የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ከኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ከሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ጋር በመሆን የታላቁ አንዋር መስጂድ አሁናዊ ሁኔታን ጎብኝተዋል። የታላቁ አንዋር መስጂድና ኻጢብ በሆኑት በሼኽ ጧሐ ሙሐመድ ሀሩንም የታላቁ አንዋር መስጂድን ታሪክና አሁናዊ ሁኔታን ለልዑኩ ገለፃ አድርገዋል።
...
ልዑኩ በታላቁ አንዋር መስጂድ በመገኘት መስጂዱን የጎበኙ ሲሆን የጁምዓ ሰላትም ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመሆን በጋራ ሰግደዋል። ዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃንም በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላት ከጀምዓው ጋር የመስገድ እድል ስላገኙ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። የአለም አቀፍ ሙስሊሞች ሊግ ልዑካን በኢትዮጵያ የጀመሩትን የስራ ጉብኘት በሌላ መርሃ ግብርም የሚቀጥሉ ይሆናል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j