Get Mystery Box with random crypto!

የሀዲያ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በዞኑ የተፈጸመውን ድርጊት በማስመልከት አጥፊዎች ለህግ ቀ | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የሀዲያ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በዞኑ የተፈጸመውን ድርጊት በማስመልከት አጥፊዎች ለህግ ቀርበው ውሳኔ እንዲያገኙ ጠየቀ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 4/2015
..
የሀዲያ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በዞኑ የተፈጸመውን ድርጊት በማስመልከት አጥፊዎች ለህግ ቀርበው ውሳኔ እንዲያገኙ ጠይቋል። በሀድያ ዞን በአንሌሞ ወረዳ በጪንጎ ቀበሌ በባለፈው የገና በአል ከተለያዩ ቦታዎች የተውጣጡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነን የሚሉ አካላት በመስጅድና በሙስሊሙ መኖሪያ ቤት በመግባት ጥቃት መፈጸማቸውን የገለጸው መግለጫው ሰዎችን በግድ ሀይማኖታቸውን እንዲቀይሩ በማለት ከ30 በላይ ሰው ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን በዝርዝር ያትታል።
...
አጥፊዎቹ ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳዩ በህግ ሒደት እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን ይህንን ጉዳይ የሚከታተሉ ኮሚቴዎች መዋቀራቸውንም አያይዞ ገልጿል። ከተጎጂዎች የሞተ ሰው አለመኖሩ የተገለጸ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ግን በወራቤ ኮ/እ ሆስፒታል በተገቢው ሁኔታ እየተከታተሉ መሆናቸውን አሳውቋል። የደቡብ ክልል መጅሊስ እና የፌደራል መጅሊስ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቋል።
..
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራ፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j