Get Mystery Box with random crypto!

የፌዴራል መጅሊሱ ልዑካን ቡድን አባላት የደቡብ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሀድያ ጥቃት ዙሪያ | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የፌዴራል መጅሊሱ ልዑካን ቡድን አባላት የደቡብ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሀድያ ጥቃት ዙሪያ ውይይት አደረጉ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 8/2015
...
የፌዴራል መጅሊሱ ልዑካን ቡድን አባላት የደቡብ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሀድያ ጥቃት ዙሪያ ውይይት አደረጉ። በውይይታቸው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመልካም አስተዳደር ዳይሬስክቶሬት ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ አብርሀም አለሙ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከዛም በተጨማሪ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተመስገን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
...
በውይይቱ ከተነሱ ቁልፍ ነጥቦች መካከል በዞኑ ተፈጥሮ የነበረውን ጥቃት በዝርዝር ያሳወቁ ሲሆን ያለውን ችግር በክልል ደረጃ ልዑካን ቡድን ተቋቁሞ እንደሚፈታም መግባባት ላይ ተደርሷል። የተነገራቸው መረጃ "ግጭት" የሚል እንደነበረ ገልጸው ጉዳዩን ግን ቦታው ድረስ መጣራት የሚያስፈልገው መሆኑን መተማመን ላይ ደርሰዋል። ኮሚቴው በቀጣይ ጉዳት የደረሰበትን ጭንጎ ወረዳ እንደሚጎበኙ ለሀሩን ሚዲያ ገልጸውልናል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j