Get Mystery Box with random crypto!

Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ harunmedia — Harun Media - ሀሩን ሚዲያ H
የቴሌግራም ቻናል አርማ harunmedia — Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @harunmedia
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.42K

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-02-23 08:03:54
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራው ልዑክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 16/2015
...
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ በሆኑት በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራው ልዑክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከተመራው የሚኒስቴር መስራቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዉይይት አድርጓል።
...
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተደረገው ውይይት

➭ በሙስሊም ተማሪዎች የሰላት ጉዳይ ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት(ዩኒቨርሲቲዎች )

➭ የሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብና ያጋጠሙ ችግሮች

➭ በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የካሪኩለም ዝግጅት እና በተማሪዎች የመማሪያ መፅሀፍት ሚዛናዊነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ዉጤታማ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ተቋማቱ ተቀራርበው ለመስራት የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
...
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሚቋቋመው እና በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በቀጣይ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የባለሙያዎች ቡድን ጋር ዉይይት ለማድረግ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
147 views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 20:27:55
1.3K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 20:27:49 ኑር የቁርዓን ባንክ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 500ሺ ቁርኣኖችን የማሰባሰብ መርሃግብር ማስጀመርያ ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው እለት ተካሔደ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 15/2015
...

ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፍቃድ በመውሰድ እንቅስቃሴ እያደረ የሚገኘው ኑር የቀርአን ባንክ እስካሁን ከ165,237 በላይ የቁርኣን ኮፒዎችን በተለየ የሀገሪቱ ክፍል ማሰራጨቱ የተገለጸ ሲሆን በአካል ያልደሩሳባቸውን ቦታዎች ደግሞ በደብዳቤ ተጠይቀው በተወካያቸው አማካኝነት ቁርኣኖችን መላካቸውን ገልጸዋል።
...
ይህን መነሻ በማድረግና ማህበሩ በተለያዩ ጊዜያት በመላው ኢትዮጵያ የገጠር መንደሮች ውስጥ ባደረገው ጥናት መሰረት በዘንድሮ የረመዳን ወር የቁርኣን እጥረቱን ለመቅረፍ 500ሺ የቁርኣን ኮፒዎችን ከመዲናችን ከአዲስ አበባ ከተማና ከአጎራባች ከተሞች ከሙስሊሙ የማህበረሰብ ክፍል በማሰባሰብ በመላው ኢትዮጵያ ለማሰራጨት ሰፊ እቅድ ይዞ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል።
...
በዚህም መሠረት ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ያህል የሚቆይ ቁርኣን የማሰባሰብ መርሃግብር በከተማችን የሚገኙ መስጂዶች የተዘጋጀ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ከ1 ጁዝ ጀምሮ እስከ 30 ጁዝ ቁርአኖችን አቅም በፈቀደ መልኩ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ መሳጂዶች በመሄድ ለኑር ቁርአን ባንክ ኢስላማዊ ማህበር ብላችሁ እንዲሰጡ ጥሪውን አቅርቧል። ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉና እና በዚህ ኘሮጀክት ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ ለሚፈልጉ ደግሞ በማህበሩ ህጋዊ የባንክ አካውንት በኩል በነየታችሁት የሙስሀፍ ቁጥር ልክ ገቢ ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

አድራሻ ኑር የቁርኣን ባንክ ኢስላማዊ ማህበር ዋና ቢሮ ፒያሳ ሶማሌ ተራ የገበያ ማዕከል 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 830 ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በጊዜያዊነት በተዘጋጁ ቢሮ በአካል በመገኘት ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።

ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.3K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 16:20:54
ዳዕዋ ቲቪ ደሴ ላይ ቅርንጫፍ ስቱዲዮ መክፈቱን በዛሬው እለት ይፋ አደረገ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 23/2015
...
የዳዕዋና የትምህርት ዘርፎች ላይ በመስራት ትኩረቱን አድርጎ በሳተላይት የሚሰራጨው ዳዕዋ ቲቪ በዛሬው እለት ደሴ ላይ ቅርንጫፍ ስቱዲዩ መክፈቱን ይፋ አድርጓል። በዛሬው እለት በደሴ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ታላላቅ ዑለሞችና እና የከተማው ህዝብ ሙስሊም በተገኘበት ደማቅ ፕሮግራምም አከናውኗል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.4K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 19:31:56
ሀሩን ሚዲያ ከሰላም የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በወንዶገነት ከተማ የሚያዘጋጀው ታላቅ የዳእዋና የሰደቃ ፕሮግራም በመጭው እሁድ ይካሔዳል።
...
ሀሩን  ሚዲያ፥ የካቲት 6/2015
...
ሀሩን ሚዲያ ከሰላም የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በወንዶገነት  የሚያዘጋጀው ታላቅ የዳእዋና የሰደቃ ፕሮግራም በመጭው እሁድ ይካሔዳል።
...
በወንዶገነት ከተማ ወሻ መስጂድ የካቲት 12/2015 ዓ.ል በሚዘጋጀው በዚህ ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ኡስታዝ ሙሀመድ ሙስጠፋን ጨምሮ የንጽጽር ዳዒው ኡስታዝ ቀመር ሁሴን፣ ኡስታዝ ካሚል ጧሃ፣ ሼይኽ ኡመር ቡሽራ እና ኡስታዝ ጧሃ ሙስጠፋ ተገኝተው ዳዕዋቸውን ያቀርባሉ።
...
የወንዶገነት ከተማና አቅራቢያ ያላችሁ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በጠዋቱ ዝግጅቱ ላይ አድትታደሙ ግብዣ ቀርቧል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.2K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 12:23:33 በጎንደር ከተማ የሚና መስጅድ ኢማምና ኻጢብ የነበሩት ሸይኽ ጀማል አደም ወደ አኼራ ሄዱ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 5/2015
...
በጎንደር ከተማ የሚና መስጅድ ኢማምና ኻጢብ የነበሩት ሸይኽ ጀማል አደም ወደ አኼራ ሄደዋል። የጎንደር ሙስሊሞች በገጠማቸው ግፍ ሁሉ ያለማመንታት ከፊት ሁነው ታግለዋል። ሸይኽ አደም በሀገር ውስጥ የዲን ትምህርትን የቀሰሙ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በውጭም በሱዳኑ አፍሪካ ዩንቨርሲቲ የተማሩ ሀፊዝ ነበሩ።
...
የጎ/ከ/ዑለ/ም/ቤትን በነጻ፣ ለሁለት ዓመታት በፀሀፊነት አገልግለዋል። ለአምስት ዓመታት የስራ አስፈጻሚ አባል ኾነው ቆይተዋል። ለውጥ ፈጥረዋል። ‹ሼህ ጀማል አደም› ቢኾንም ስማቸው፣ በ“ሼህ ጀማል ገበሬው” ነው የሚታወቁ። በእርግጥም! የነህው፣ የሶርፍ፣ የመንጢቅ፣ የሉጛ ገበሬ ነበሩ። የዲን ገበሬ ነበሩ። በወሎና በጎንደር፣ እንዲሁም በሱዳን ሀገር ተዟዙረው ሰፊ ዒልም ያካበቱ ታላቅ ዓሊም ነበሩ።
...
ሼህ ጀማል ከወራት በፊት ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው በትናንትናው ዕለት ለህልፈት በቅተዋል። መልካም ስራቸውን አላህ ይቀበላቸው። ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእኛም መፅናናት ይኹን። አላህ መልካሙን ተተኪ ይስጠን
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
434 views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 12:23:30
430 views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 20:53:29
1.2K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 20:53:22 አልማሂር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ኦላንይን የቁርአን ውድድር!

Al-Maher International Ethiopian Online Qur'an Contest
...
❐ በጃዕፋሩ ጦያር እና ቲብያን የቁርአን ሒፍዝና የተርቢያ ማዕከሎች እንዲሁም በሃሩን ሚዲያ የጋራ ትብብር የሚዘጋጅ እና በአለም ዙሪያ የሚገኙ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ውድድር ሲሆን ውድድሩም በርካታ ተከታታይ ባላቸው አፍሪካ ቲቪ፣ ሐሚልተን ቲቪ ፣ ዳዐዋ ቲቪና በሃሩን ሚዲያ ረመዳን ወሩን ሙሉ በእኩል ሰዓት የሚተላለፍ ይሆናል።
...
አልማሂር ኦንላይን የቁርኣን ውድድር በአይነቱ ልዩ የሆነው ታላቅ አለማቀፍ የኦላንይን የቁርአን ውድድር ያዘጋጀ ሲሆን ምዝገባ መጀመሩን ሲያበስር በላቀ ደስታ ነው!!
...
ይህ ውድድር፣ የተለያዩ መርከዞች በጋራ ለኢስላም፣ ለሙስሊሙ ማህበረስብ እንዲሁም ለሀገር ግንባታ በትብብር መስራት እንዲችሉ፣ አቅም ያላችው ሁፋዞች ቦታ ሳይገድባቸው መወዳደር እንዲችሉ እንዲሁም በተለያየ ቦታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ከማስተሳሰሩም በተጨማሪ የሚከተሉትን ዓላማዎችን ያነገበ ታላቅ ፕሮግራም ነው።
...
በአልማሂር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ኦንላይን የቁርኣን ውድድር ላይ ለመሳተፍ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፦

➭ ተወዳዳሪው ኢትዮጲያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጲያዊ የሆነ

➭ ለወንድ ተወዳዳሪዎች 30 ጁዝ ቁርኣንን በሙሉ የሐፈዘ ሲሆን ለወንድ ተወዳዳሪዎች የእድሜ ገደብ የለውም።

➭ ለሴት ተወዳዳሪዎች እስክ 15 ጁዝ ቁርኣንን የሐፈዘች እና እድሚያችው 14 እና ከ14 አመት በታች።

➭ በመመዝብያ ቀናት ውስጥ ብቻ መመዝገብ የሚችል

➭ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚችል የውድድር ሰዓትን ማክበር እና ኢስላማዊ አደቦች መላበስ የወድድሩ ደንቦች ናቸው።
...
ይህ ታላቅ ውድድር በወርሃ ረመዳን ለ30 ቀናቶች በ4ቻናሎች የሚተላለፍ መሆኑን እየገለፅን ምርትዎንና አገልግሎትዎን እንዲያስተዋውቁ ተጋብዘዋል። ይሄን የተከበረን ውድድር በመደገፍ የዱንያን እና የአኺራን ጥቅም ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ ቀርቦለዎታል።
...
በዚህ ኦላንይን የቁርአን ውድድር ላይ ለመሳተፍ ምዝገባው የሚካሔደው ከጥር 25 እስከ የካቲት 7/2015 ዓ/ል ድረስ ነው።

ለመመዝገብ

https://forms.gle/ya3JFzZhXApBurbZ6

https://t.me/almaherqurancompetition

ለበለጠ መረጃ

0931315455
0927405576
0911422820

ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
1.3K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 10:29:01
2.2K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ