Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራው ልዑክ ከኢ | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራው ልዑክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 16/2015
...
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ በሆኑት በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራው ልዑክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከተመራው የሚኒስቴር መስራቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዉይይት አድርጓል።
...
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተደረገው ውይይት

➭ በሙስሊም ተማሪዎች የሰላት ጉዳይ ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት(ዩኒቨርሲቲዎች )

➭ የሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብና ያጋጠሙ ችግሮች

➭ በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የካሪኩለም ዝግጅት እና በተማሪዎች የመማሪያ መፅሀፍት ሚዛናዊነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ዉጤታማ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ተቋማቱ ተቀራርበው ለመስራት የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
...
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሚቋቋመው እና በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በቀጣይ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የባለሙያዎች ቡድን ጋር ዉይይት ለማድረግ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j