2023-02-27 15:52:10
በኢስላማዊ ተቋማት ምዝገባ፣አገልግሎት አሰጣጥ ናአስተዳደር መመሪያ ላይ ስልጠና ተሰጠ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 20/15
...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኢስላማዊ ተቋማት ምዝገባ፣ አገልግሎት አሠጣጥና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 01/2015 ላይ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ፣ ከአዲስ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች የሁለት ቀን የስራ ላይ ስልጠና በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሠብሠቢያ አዳራሽ ተሰጠ።
...
ስልጠናውን በቁርዓን በሼይኽ ያዕቁብ አብዱል ለጢፍ የተከፈተ ሲሆን በኢስላማዊ ተቋማት ምዝገባ ፣አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር በመመሪያ ቁጥር 01/2015 ላይ በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተዋረድ ለሚገኙ ባለሙያዎች እና ለባለ ድርሻ አካላት መሠጠት የተጀመረው ይህ ስልጠና የሚቀጥል መሆኑን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ከማል ሀሩን በስልጠናው መክፈቻ ላይ ገልፀዋል።
...
በዘርፉ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለያዩ ጊዚያት የድጋፍ ደብዳቤ ወስደው በስራ ላይ የሚገኙ እንዲሁም ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የኢስላማዊ ተቋማት ምዝገባ፣አገልግሎት አሰጣጥ ና አስተዳደር ዳይሮክቶሬት በቅርቡ ለአገር በቀልና ለውጪ ሀገር የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ማኅበሮች ፣የወቅፍ እና ጊዚያዊ ኮሚቴዎች መመዝገብ በቅርቡ እንደሚጀመር እና የምዝገባ ጥሪውን በጠቅላይ ምክር ቤቱ በይነ መረብ አማካኝነት ጥሪ እንደሚደረግ ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።
...
የኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንደ አዲስ በአዋጅ ቁጥር 1207/2012 ከተቋቋመ በኋላ የኢስላማዊ ተቋማት ምዝገባ ፣አገልግሎት አሰጣጥ ና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 01/2015 በጠቅላይ ምክር ቤቱ ታሪካዊ ያደርገዋል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
2.0K views12:52