Get Mystery Box with random crypto!

በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስተባባሪነት የሰላምና የአንድነት | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስተባባሪነት የሰላምና የአንድነት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ የካቲት 22/2015
...
በዛሬው እለት የካቲት 22 /2015 ተጀምሮ እስከ ነገ የሚቆይ በቻግኒ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስተባባሪነት የሰላምና የአንድነት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የእለቱ የክብር እንግዳ እና የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጀውሀር ሙሀመድ የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ከመጅሊሱ የክልሉ የዳእዋና የትምህርት ዘርፍ፣ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪዎች የምስራቅ ጎጃምና ምእራብ ጎጃም ዞን መጅሊስ ተወካዮች ተገኝተዋል።
...
የአዊ ብሄረሰብ ዞን የሀይማኖት ጉዳዮች ግጭት አስወጋጅ አቶ ሞገስና የሰላምና ደህነት ምክትል አቶ ሙሉአለም ዘሪሁን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎችም የመንግስት ሃላፊዎች በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ሲሆን ከዑለሞችም ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዘኽረዲን ኸሊልና ሸይኽ ሙሀመድ አወል በፕሮግራሙ ላይ ታድመዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j