Get Mystery Box with random crypto!

የአለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ከሶስት አስርተ አመት በኋላ አወሊያን ጎበኘ .. ሀሩን ሚዲያ፥ ጥ | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የአለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ከሶስት አስርተ አመት በኋላ አወሊያን ጎበኘ
..
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 2/2015
...
ከሰባ ሀገራት በላይ በትምህርት በጤና እና በልማት የበጎ አገልግሎት ስራው የሚታወቀው አለም አቀፉ የሙስሊሞች ሊግ ከሶስት አስርት አመት በኃላ የአወሊያን አሁናዊ ሁኔታን በልዑኩ አማካኝነት በተቋሙ በመገኘት ጉብኝት አካሂዷል።
...
ልዑኩ በሊጉ የአውሮፖ እና በአሜሪካ ዋና ዳሬክተርና የኢስላሚክ ሊግ የዋና ፀሐፊዉ አማካሪ በሆኑት በዶክተር አብዱል አዚዝ ሰርሃን የተመራ ሲሆን ሊጉ ለአስርት አመታት ሲያስተዳድር የነበረውን አወሊያን ለአለም አቀፉ ኢስላማዊ ዕርዳታ ድርጅት አስረክቦ ከሀገር ከወጣ ከ ሶስት አስር አመት በኃላ በልዑካን ደረጃ ሲጎበኝ ይህ የመጀመሪያው ነው።
...
የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ጀማል መሐመድ እና የአወሊያ ስራ አስኪያጅ በሆኑት ሀጂ ሰዒድ አስማረ አማካኝነት የአወሊያን አሁናዊ ሁኔታን ለልዑኩ ገለፃ ተደርጎላቸዋል። የአለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ የዋና ፀሐፊዉ አማካሪና የልዑካኑ መሪ ዶክተር አብዱላዚዝ ሰርሃን በአወሊያ ማህበረሰብ የተደረገላቸውን ልዩ የሆነ አቀባበል መደሠታቸውን ገልፀው በቀጣይ ከአወሊያ ጋር አብሮ ለመስራት ከሚመለከተው አካል ጋር ዉይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል። ዛሬ በተደረገው የልዑኩ ጉብኝት ላይ የአወሊያ መስጂድ ኢማም የሆኑት ሼህ ዑመር መሐመድ ወሌን ጨምሮ የአወሊያ የማህበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።
...
ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራ፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j