Get Mystery Box with random crypto!

የጠቅላይ ምክር ቤቱ አገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር ተጀመረ ... ሀሩን ሚዲያ፥ መጋቢት 6/2015 | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የጠቅላይ ምክር ቤቱ አገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር ተጀመረ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ መጋቢት 6/2015
..
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መሠብሰቢያ አደራሽ አገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር እየተካሄደ ይገኛል። ፕሮግራሙን በቁርዓን ቃሪዕ ሙከሚል ከማል አብደላ ከፍቶታል።
...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ዛሬ በሚደገው አገራዊ የቁርዓን ውድድር መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር የማድረግ እድል አላህ ሱ.ዉ ስለሰጣቸው ምስጋናቸውን ገልፀዋል።
...
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይህንን መሰል የቁርዓን ውድድር ስኬት የበኩሉን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ለዛሬ የቁርዓን ተወዳዳሪዎች እዚህ መድረስ ድጋፍ ላደረጉ ወላጆች፣ መሻይዒኾችና መድረሳዎች ምስጋናቸው አቅርበዋል።
...
በዛሬዉ 2015/1444 የአገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር ላይ ሰላሳ ተወዳዳሪዎች ብርቱ ውድድር የሚያደርጉ ሲሆን አሸናፊዉ በዱባይ በሚካሔደው አለም አቀፉ የቁርዓን ውድድር ላይ ኢትዮጵያ ወክሎ ይወዳደራል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j