Get Mystery Box with random crypto!

የኢድ ሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሀይል አስታወቀ ... | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የኢድ ሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሀይል አስታወቀ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 13/2015
...
የ1ሺህ 444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት ስነ ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
...
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አልፈጥር በዓል የሶላት ስነ ስርዓት በርካታ ህዝበ ሙስሊም በተገኘበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ተካሂዷል።
...
ከንጋት ጀምሮም ወደ ሶላቱ ቦታ በሚደረግ ጉዞም ሆነ የሶላት ስነስርአቱ በሚካሄድበት ወቅት አንዳችም በዓሉን የሚያውክ ሁኔታ እንዳይፈጠርና የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም የፀጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣታቸው ተመላክቷል።
...
በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት እንደነበረው የማስተባበሩን ሚና በመወጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ነው የተገለፀው።
..
በዚህም የአዲስ አበባ ነዋሪን ጨምሮ የሶላት ስነ ስርአቱ በሚካሄድበት ስፍራ በመገኘት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል ምስጋና አቅርቧል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j