Get Mystery Box with random crypto!

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለመስገጃ የሚሆን 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦ | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለመስገጃ የሚሆን 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሰጠቱን ዛሬ አስታውቋል።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 13/2015
...
የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ዛሬ የኢድ አልፈጥር በዓል በባህር ዳር ስታዲየም በሚከበርበት ወቅት ነው ይህንን ዜና ማብሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
..
ዶ/ር ድረስ ሳህሉ እንደተናገሩት "ለብዙ ጊዜ ስትጠይቁት የነበረ የመስገጃ ቦታ አሁን በክልልም ፀድቆ የመጣ ስለሆነ ምናልባትም በሚቀጥለው ዓመት በደንብ ሰርታችሁት እዚህ ሳይሆን እዛው ከተፈቀደላችሁ ቦታ ላይ የምታከብሩት ይሆናል። ክልሉ ያቀረባችሁትን ጥያቄ እኛ አፅድቀን ልከን ክልሉም ተቀብሎት 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የኢድ አልፈጥር በዓል የምናከብርበት ቦታ ተፈቅዷል። " ብለዋል።
...
ከንቲባው ይህንን ንግግራቸውን ሲያደርጉ የባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ምእመን እጅግ በደስታ ስሜት ተክቢራውን አሰምቷል።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j