Get Mystery Box with random crypto!

የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ-አል ፈጥር በዓልን ሲያከብ | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ-አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር በረመዳን ወቅት የነበረውን የመረዳዳትና የአብሮነት እሴቱን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስታወቀ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 12/2015
...
የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1444ኛው የኢድ-አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በወራቤ ከተማ በሚገኘው ጊዜያዊ ጽህፈት ቤት አስተላልፏል፡፡
...
የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሀጂ ሙሃመድ ከሊል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1444ኛው አመተል ሂጅራ ጾም ፍች የእንኳን አደረሳችሁ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
...
ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ውስጥ በርካታ በጎ ተግባራትና ከፈጣሪያቸው ጋር የሚያቀራርቡቸውን የአምልኮ ስርዓቶች በከፍተኛ መነሳሳት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው ይህንን በጎ ተግባር ከረመዳን ፆም በኋላም አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
...
የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጸሃፊ ሼህ ኡስታዝ ሳዲቅ ወጌቦ በበኩላቸው ህዝበ ሙስሊሙ ጾም ማገባደጃ ላይ እንዲያወጣ ግዴታ የሆነበትን ዘካቱል ፈጥር በግዜው እና በአግባቡ ማውጣት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j