Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዬች ከፍተኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት የተመራ ልኡካን ቡድን በደብረ ብር | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዬች ከፍተኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት የተመራ ልኡካን ቡድን በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዬች ድጋፍ አደረገ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 20/2015
...
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከከተማች ፣ከሀገራችን እና በወጭ ሀገር ከሚኖሩ ሙስሊሞች ያሰባሰበውን ከ5 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት ምግብ፣ አልባሳት፣የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፉን አድርጎል።
...
ድጋፉን ለማድረስ በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዬች ከፍተኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት ሼህ ፈትሁዲን ሀጂ ዘይኑ ሙቅና እና የስራ አስፈፃሚ አባልና የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሊድ መሀመድ ከነጃሺ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ ኸይር ፈላጊ የበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲሁም ተአውን የልማትና መረዳጃ እድር አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ደብረ ብርሃን ሲደርሱ ም/ከንቲባው ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
..
ልኡከካን ቡድኑ ሁለት መጠለያ ካምፖችን ከጎበኝ እና ድጋፉን ለማህበረሰቡ ካደረሰ በኃላ ከደብረ ብርሃን ከተማው እስልምና ጉዳዬች ጋር ምክክር በማድረግ ጉዳዩ በቀጣይ መጪው ግዜ ክረምት ከመሆኑ አንጻር እንዲሁም የቲም ህፃናት በስፍራው ስለሚገኙ ትኩረት ተሰጥቶ በጋራ የማህበረሰባችንን ችግር ለማቀለል በቀጣይነት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
...
ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j