Get Mystery Box with random crypto!

የውጪ ኦዲት ምርመራን ግኝት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ። .. | Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

የውጪ ኦዲት ምርመራን ግኝት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዚያ 8/2015
...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምክር ቤቱን የፋይናንስ አሰራርን ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

ከነዚህም ውስጥ ፦
1ኛ. በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋምና የልማት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤትን ከጥር 1/2012 እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ል የሁለት አመት ከሰባት ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴን እንዲሁም

2ኛ. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱን ከታህሳስ 1/2012 እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ል የሁለት አመት ከስምንት ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴን በሰርቲፋይድ ቻርተርድ አካውንታንት በሆኑና ሕጋዊ የሙያ ፍቃድ ባላቸው በውጪ አዲት የፋይናንስ እንቅስቃሴያቸውን ለማስመርመር ግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ባወጣው መሠረት የኦዲት ምርመራ ስራቸውን በማጠናቀቅ የኦዲት ግኝት ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም በውጪ የኦዲት ተቋሙ የኦዲት ምርመራው ግኝት ሪፖርተርን መሠረት በቀጣይ ተጠያቂነት መሠረት ባደረገ መልኩ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የወጪ የኦዲት ተቋሙ የፋይናንስ ግኝት ምርመራ መሠረት በማድረግ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚወሰዱ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
...
መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።

ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j