Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-01-16 15:28:21
እንደ ፎርብስ ዘገባ ከ180 ሚሊየን ዶላር በላይ ንብረት ያፈራው ፡ የ25 አመቱ ፈረንሳዊው የእግር ኳስ ኮከብ Kylian Mbappe አሁን የናፈቀው ወጣትነቱን በነጻነት መኖር ነው ።

ፈርምልኝ ፡ አብረን ፎቶ እንነሳ ሳይባል ፡ መጣ ሄደ ፡ በዚህ አለፈ ፡ ሳይባል በነጻነት መንቀሳቀስና ፡ መኖር ናፍቆታል ዝና እና እውቅናው ፡ ከምቾት ይልቅ ሰላሙን ነስቶታል ። " እንደ ማንም ሰው ዳቦ ቤት ሄጄ መግዛት እፈልጋለሁ ።

በምፈልገው ሬስቶራንት በፀጥታ መመገብ መቻል ናፍቆኛል ። ከጓደኞቼ ጋር ማንም መጥቶ ሳይረብሸኝ ፓርቲ ወጥቶ መዝናናት ፡ ይህንና ይህን መሰል ለሰው ቀላል የሚመስሉ ሰውኛ ነገሮችን ማድረግ ብፈልግም በዚህ ወቅት ይህ ነገር ለኔ ምኞት ብቻ ሆኗል ። በርግጥ ይህ ነገር ለአብዛኛዎቹ ሰወች ቀላል ወይም ተራ ነገሮች ቢሆኑም ለኔ ግን ምኞት ብቻ ሆኖ ቀርቷል ። እናም እንደ ማንም ሰው መንቀሳቀስ የምችልበት ነገር ቢኖር ምንም አይነት ገንዘብ ብከፍል አይቆጨኝም ። ሲል ተናግሯል ።
......
የአንዱ ትልቅ ምኞት ፡ ለአንዱ ተራ ነገር ነው

Wasihune Tesfaye

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K viewsedited  12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-06 08:20:14 #Update

ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ማለቱ ይታወሳል።

ይህ ተከትሎ አንዳንድ ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ ካደረጉት ውስጥ አንዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው።

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ባደረገው ጥሪ ፤ የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ እና የማታ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ከጥር 15-17/2016 ዓ.ም ወደ ተቋማቸው እንዲገቡ ብሏል።

በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ (Freshman፣ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላቸው ተማሪዎ ከጥር 21-23/2016 ዓ.ም ወደ ተቋማቸው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎቹ የ2016 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ ጥር 6 እና 7/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በዚህ ጥሪ መሰረት ፤ ነባር የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ትምህርታቸው ሲከታተሉ የቆዩና የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ በ2014 ዓ.ም እና በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal በመሙላት ያቋረጡ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት አምጥተው ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ብሏል።

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ እስከሚደረግ በትዕግስት እንድጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ነባር ተማሪዎቹ ጥር 2 እና 3/2016 ዓ.ም ምዝገባ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቅርቧል።

ለአንደኛ ዓመት እና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ እሰከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሌሎች በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

በአማራ ክልል ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች አስር ሲሆን በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን ሳይጠሩ ወራትን አስቆጥረዋል።

ተማሪዎች መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በተለያዩ መንገዶች ጭና ሲፈጥሩ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዩኒቨርሲቲዎች ከጥር 1 አንስቶ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት እንደሚጀምሩ ማሳወቁ አይዘነጋም።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-01 08:07:04
January 1,2024

በግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠር አዲሱ ዓመት 2024 ገብቷል።

እጅግ በርካታ ሀገራት አዲሱን ዓመት 2024 እየተቀበሉ ይገኛሉ።

ከዓለማችን ሀገራት መካከል የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ያላት #ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምትነት የምትነሳ ሲሆን ሀገራችን የግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠርን እንደ ዘመን መለወጫ አትጠቀምም።

የ13 ወራት ፀጋ ባለቤቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት የዘመን አቆጣጠሯ መለየቱ ብቻ ሳይሆን የራሷ የሆኑ ባህሎች፣ ቋንቋዎች ፣ ፊደል፣ ጥበብ ያለባት ሀገር ናት።

#tikvagethiopia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.9K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-20 21:04:34
" ለአላህ ብላችሁ ተባበሩኝ እያለቀስኩ ነው…ልጄ ልትገደልብኝ ነው አስመጡልኝ " - አረጋዊያኖቹ የለይላ  አባትና እናት

ከአሰሪዎቿ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ግጭት ተፈጥሮ በመካከል የአንድ ታዳጊ ሕይወት በማለፉ በሳዑዲ መንግሥት ሕግ መሠረት የሞት ፍርድ የተፈረደባት ኢትዮጵያዊት የሟች ቤተሰቦች የሞት ፍርዱ ወደ ካሳ እንዲቀየር ተስማምተዋል።

በዚህም የተጠየቀው 2 ሚሊዮን ሪያል ከወዳድ ዘመድ ተሰብስቧል። ይሁን እንጂ ገንዘቡ ቢሰበስብም የሚላከው በመንግሥት በኩል በመሆኑና ገና ስላልተላከ ፍርደኛዋ በሳዑዲ የሞት ፍርድ እየተጠባበቀች መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቿ ገለጻ ተረድቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አረጋዊ የፍርደኛዋ አባት አቶ ኑርሰቦ፣ " ለአላህ ብላችሁ ተባበሩኝ #እያለቀስኩ ነው። እናቶች፣ አባቶች እባካችሁ ተባበሩኝ። የኢትዮጵያ ልጆች፣ የዓለም ልጆች ተባበሩኝ እባካችሁ ትመጣልኛለች እያልኩ 11 ዓመታት ሙሉ ጠበኳት እባካችሁ " ሲሉ እንባቸውን እያፈሰሱ ተማጽነዋል።

" ልጄን ልትገደልብኝ ነው አስመጡልኝ " ያሉት፣ የፍርደኛዋ አረጋዊት እናት ወ/ሮ ነፊሳ ሙሳ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከወዳጅ ዘመድ የተሰበሰበውን ገንዘብ በባንክ በኩል ወደ ሳዑዲ መንግሥት በፍጥነት በመላክ ልጃቸውን ከሞት እንዲታደግላቸው በአጽንኦት ጠይቀዋል።

የ21 ዓመቷ ለይላ ኑርሰቦ ሰርቸ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑድ አረቢያ ከወጣች 11 ዓመታትን እንዳስቆጥረች ወላጆቿ አስረድተዋል። 

ይሁን እንጂ በሳዑዲ አረቢያ ከአሰሪዎቿ ጋ በተፈጠረ ግጭት የ11 ዓመት ታዳጊ በፀቡ ወቅት በመጎዳቱ  #ለአምስት_ወራት በሆስፒታል ሲረዳ ቢቆይም ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም።

ይህን ተከትሎም 'የገደለ ይገደል' በሚል የሳዑዲ ሕግ ለይላ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ለ11 ዓመታት እስራትና የሞት ፍርድ እንደተፈረደባት ቤተሰቦቿ እንዲሁም የቲም ለይላ አስተባባሪዎች ገልጸዋል።

እንደ ገለጻው ከሆነ፣ የሟች ቤተሰቦች የሞት ፍርድ በካሳ ክፍያ እንዲቀየር ተስማምተዋል።

በዚህም 2 ሚሊዮን ሪያል፣ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ ደግሞ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፈላቸው ተብሎ በሳዑዲ መንግሥት ውሳኔ ተላልፎበታል።

ወዳጅ ዘመድ፣ በጎ አድራጊ ድርጆቶች ድጋፋ እንዲያደርጉ በማኀበራዊ ሚዲያ በተደረገ የ54 ቀናት ዘመቻ በቤተሰቦቿ በኢትዮጵያ በተከፈተ የባንክ አካውንት 30 ሚሊየን ብር፣ በሳውዲ በሟች ቤተሰቦችና በፍርደኛዋ በተከፈተ የባንክ አካውንት 230,000 ሪያል ተሰብስቧል።

መንግሥት የተሰባሰበውን ገንዘብ በፍጥነት ካልከ #ከ39 ቀናት በኋላ ለይላ የሞት ፍርዱ ሊፈጸምባት እንደሚችል በመግለጽ ቤተሰቦቿ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተማጽነዋል።

በዛሬው ዕለት በሸራተን ሆቴል በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ የ'ለይላን እንታደጋት' የሶሻል ሚዲያ ንቅናቄ፣ "በሳዑዲ የሞት ፍርድ የተፈረደባት እህታችንን እንታደጋት" የሚል ጥሪ ተላልፏል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.2K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-13 13:43:40
አርቲስት ሀናን ታሪክ 10,000,000.00 ብር ተከፈላት

አርቲስት ሀናን ታሪክ የብራንድ አምባሳደር በመሆን ለ2 አመት አስር ሚሊዮን ብር ተከፈላት።

ሀናን ስምምነቱን ያደረገችው ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ ታዋቂና ግዙፍ የቻይና ኩባንያ ጋር ነው፡፡

ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ያቋቋመ ሲሆን በዚህም ‹‹ኤስ›› በሚል ብራንድ ያልተለመዱና አዳዲስ የታሸጉ የኬክ ወይንም የጫፋጭ ምግቦችን እያመረተ በመላው አገሪቱ እያከፋፈለ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ይህንን ‹‹ኤስ›› የተሰኘ ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማሳደግ የአንድ አመት የኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን እቅድ ማውጣቱን ገልጿል፡፡

በዚህ እቅዱ ውስጥም ታዋቂዋን አርቲስት ሀናን ታሪክን ማካተቱን አስረድቷል፡፡ ‹‹የኤስን ብራንድ ፕሮሞሽን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ አርቲስት ሀናን እንደምትጠቅመን አምነንበታል›› ብሏል ድርጅቱ፡፡

ይህን የ10ሚሊዮን ብር ስምምነት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አከናውናለች።

ይህ ክፍያ በኢትዮጵያ ብራንድ አምባሳደርነት ታሪክ ሪከርድ የሰበረ ሆኗል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-02 17:23:58 ካናዳ በቀጣዩ የፈረንጆቹ አመት  50,000 ኢትዮጵያንን  ወደ ሀገሯ ለስራ ለትወስድ ትችላለች

ፊደል ፖስት   ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው  ሰዎች የሰማው መረጃ ይሄን ይመስላል;

እነማን ነው የሚሂዱት?

ዘጠኝ ሙያዎች የተለዩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ፣ የምግብ ምርት  ማምረትና ማቀነባበር እና ማሸግ፣  አናጢነት ፣ የኤሌትሪክ ባለሙያ ፣ ነርሲንግ ፣ የኤርፖርት አስተናጋጅ ፣  ኮምፒዊተር ሳይንስ እና አይቲ  የሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚፈለጉ ይሆናል።

ለመሄድ ምን ያስፈልጋል ?

በነዚህ ሙያዎች የሰለጠነ ባለሙያ   በኦንላየን እና  በአካል  ፈተና እዚሁ ኢትዮጰያ ውስጥ  ይፈተንና  ፈተናውን ካለፈ / ች  ካናዳ ካሉት ከቀጣሪ ድርጅቶቹ ጋር ወደ ሚያገናኙት፣ የፓስፖርትና አስፈላጊ ፎርም  ወደ ሚሞሉለት የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ተልኮ  የጉዞው ሂደት ተጀምሮለት በአጭር ጊዜ ይሄዳል።

መቼ ይጀመራል?

የወረቀት ስራዎች የተጀመሩ ሲሆን በቅርቡ በኢትዮጵያና በካናዳ መንግስት በኩል  የሰለጠነ ባለሙያ ወደ ካናዳ በመላክ ጉዳይ ላይ  የመግባቢያ ሰነድ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።

በካናዳ ያለው  Ministry of Labour, Training and Skills Development,  የኢሚግሪሽን  ቢሮ እና የካናዳ መንግስት   በጉዳዩ ላይ ማብሪሪያ ተሰጥቷቸው ጉዳዩንም አምነውበታል። 

በኢትዮጵያ በኩል  የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር  ስራውን ተግባራዊ ለማድረግ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ጋር እየሰራ ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.4K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-24 18:57:14
"አይጥ" የግብፅን ባለስልጣን ከስራ አስባረረች!

አንድ የግብጽ ከፍተኛ የስራ ኃለፊ በአይጥ ምክንያት ከስራ ገበታቸው መባረራቸው ተነግሯል።

የግብፅ የትራንስፖርት ሚኒስትር ካሜል አል ዋዚር የሀገሪቱን የባቡር ኩባንያ የተቀናጀ አገልግሎት፣ የጽዳት እና የአስተዳደር መድህን ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ሳሚ አብደል ተዋብን ነው ከሰልጣን ያነሱት። ባለስልጣኑ ከስራቸው የተሰናበቱት በሩሲያ ሰራሽ ቅንጡ ባቡሮች ውስጥ አይጦች በመገኘታቸው ነው ተብሏል።

ካይሮ 24 ኒውስ የተባለ ድረ ገጽ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ምንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ ኃፊው ከሰልጣናቸው እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈው ባሳለፍነው ማክሰኞ ነው። እርምጃው የተወሰደውም በሩሲያ ሰራሽ ቅንጡ ባቡሮች ውስጥ አይጦች እንዳሉ የሚያሳይ የቅሬታ ቪዲዮ መለቀቁን ተከትሎ እንደሆነም ተነግሯል።

በዚህም ባቡሩ ውስጥ በሩሲያ ሰራሽ ባቡሮች ውስጥ ውስጥ ደካማ ንፅህና እና ደህንነት በመኖሩ ባለስልጣኑ ከኃላፊነታቸው ተባረዋል።በሉክሶር- ካይሮ የባቡር መስመር ውስጥ አይጦች መኖራቸውን ተሳፋሪዎች ቅሬታ ማቅረባቸውንም ምንጮቹ አስታውቀዋል።አይጦች ከአንድ በላይ ባቡር ውስጥ ታይተዋል የተባለ ሲሆን፤ ይህም በተሳፋሪዎች ላይ ድንጋጤ እና ቅሬታ የፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.8K viewsedited  15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-20 21:32:55
ጥንቃቄ ለወላጆች!

15 አመቱ ነው። ሳቢር ሬድዋን። አጋቾች ከቤት አባብለው አውጥተውት ካገቱት በኋላ ቤተሰቡን ከፍተኛ ብር ጠይቁ። ገዳዮቹ ገንዘብ እንኳን እስኪሰበሰብ አልጠበቁም። በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውት ሲያበቁ በሸገር - ጣዊል ሪልስቴት አካባቢ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ጥለውት ተሰውረዋል።

ሟች ተማሪ ሳቢር ሬድዋን ከአንዲት ሴት በተደጋጋሚ ስልክ ሲደወልለት እንደነበር። ደዋይዋ ደብዳቤ ልታደርስልኝ ስለምፈልግ ስልክህን ይዘህ ውጣ እንዳለችው ታውቋል፡፡ ሳቢር ስልክ ሳይዝ ደዋይዋ ወዳለችበት ቦታ መሄዱንና እዚያው መታገቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንዲህ አይነቱ ወንጀል ተስፋፍቶ የስራ እድል እስከመሆን ስለደረሰ ወላጆች ከባድ ጥንቃቄ ሊያርጉ ይገባል።

Zehabesha

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.7K viewsedited  18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-16 13:06:57
ቻይና የዓለማችን ፈጣኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ስራ ላይ አዋለች

ቻይና በሰኮንድ 1 ነጥብ 2 ቴራባይት ፍጥነት ያለው ዓለማችንን ፈጣኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ስራ ላይ አውላለች፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሰኮንድ 150 ፊልሞችን መላክ የሚያስችል የዓለማችን ፈጣኑ ኢንተርኔትም ነው ተብሏል፡፡

"ሁዋዌ" እና "ቻይና ሞባይል" የተሰኙት ሁለት ኩባንያዎች በጋራ ስራ ላይ ያዋሉት ይህ የኢንተርኔት አገልግሎት በሰኮንድ 1 ሺህ 200 ጊጋ ባይት ፍጥነት ያለው ነው፡፡

ፈጣኑ የኢንተርኔት አገልግሎት ከቤይጂንግ ወደ ጉዋንዡ ከተማ በተዘረጋ 300 ኪሎሜትር ኦብቲክ የፋይበር መስመር ነው አገልግሎት ላይ የዋለው፡፡

አገልግሎቱ ይጀምራል ተብሎ ከተገመተበት ሁለት አመት አስቀድሞ ስራ ላይ መዋሉም ተጠቅሷል፡፡

አሁን ላይ አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ያለው የኢንተርኔት ፍጥነት ከ100 እስከ 400 ባይት በሰኮንድ ነው፡፡

አሁን ቻይና ስራ ላይ ያዋለችው በሰኮንድ 1 ነጥብ 2 ቴራ ባይት ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት ለቤት አገልግሎት አይውልም መባሉን አሪራንግ ዘግቧል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K views10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-11 20:07:52
ሰው ሠራሽዋ ዜና አንባቢ በኢትዮጵያ!

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዜና አቅራቢዎችን በይፋ ማስተዋወቅ ጀምሯል።ይች በምስሉ ላይ የምትታየው ሮቦት በቅርቡ  ዜና የማቅረብ ስራዋን ትጀምራለች ተብሏል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.1K viewsedited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ