Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-11-03 18:38:56 የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በኹሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግሥት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም መሠረት፦
የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 255 ያመጡ

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 -234 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600- 218 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 200 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 224 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 192 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ  ተማሪዎች  ከ600 - 180  ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180  ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።
___

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.7K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-02 07:27:08
በአሜሪካ ቤቷን ሰብሮ ሶፋ ላይ በድፍረት የተኛውን  ሰው  ያገባችው  ሴት አነጋጋሪ ሆናለች

ነገሩ እንዲህ ነው;

ካትሪን የተባለችው የኒው ዮርክ ነዋሪ ከስድስት አመት በፊት  አንድ ቀን ጠዋት ስትነሳ ቤቷ ሳሎን  አንዱ  መስኮት  ተሰብሮ  ተመለከተች ።  ሳሎን  ትልቁ ሶፋ ላይ የተኛ  የሚያንኮራፋ የወንድ  ልጅ ድምፅ ሰማች። ደነገጠች።

ቤቷ ከእህቷ በቀር  መጥቶ የሚተኛ እንደሌለ ታውቃለች።

እህቷ ጋር ስትደውል እንዳልመጣች እና ቤተሰብ ጋር እንዳደረች ነገረቻት ።

ፖሊስ ጠራች ። ሰውዬው ከተኛበት ተቀሰቀሰ ። በሰጠውም ምላሽ ማታ ክለብ እንደነበረና  ጠጥቶ ስለነበረ   እንዴት እንዲህ እንዳደረገ እንደማያውቅ ተናገረ።

ካትሪን ቤቷን ያለውን ዕቃ ሁሉ አበጥራ ፈተሸች። ምንም የተወሰደ ነገር የለም።


ሚካኤል ጆንስተን የተባለው ሰው ወደ ጣቢያ ተወሰደ ። ካትሪን ሰወዬው እንቅልፍ ጥሎት ይሆናል ቤቴ መጥቶ የተኛው በማለት መክሰሱን ተወችው።

ሚካኤል ጆንስተን  ከፖሊስ ጣቢያ  ከተለቀቀ በኃላ   በአንዱ ቀን ያደረገውን ነገር  በቀና ተመልክታ የሰራውን ወንጀል  ይቅርታ በማለቷ  ልብ የሚነካ የምስጋና ደብዳቤ ከአበባ ጋር ለካትሪን ላከላት።

ካትሪን  ከሰውዬው ጋር  መቀራረብ ጀመረች  ። ቅርርባቸው አድጎ ሰሞኑ እንደተጋቡ  ዴይሊ ኒዮርክ ዘግቧል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.9K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-28 20:33:46 ዛሬ ምሽት 4 :35 ላይ ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ እንደሚታይ ተነገረ

ዛሬ ምሽቱን ጨረቃ የተወሰነ ከፊል አካሏ የመሬት ጥላ ሲያርፍበት እንደሚሸፈንና  ይህም ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ እንዲከሰት እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጄኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ግርዶሹ ዛሬ ምሽት ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም በሁሉም የአፍሪካ ክፍል ይታያል የተባለ ሲሆን ከፊል ግርዶሹ ከምሽቱ 4:35 ጀምሮ ምሽት 5:53 ላይ እንደሚያበቃ የተገለጸ ሲሆን፤ 6 በመቶ የሆነው ዋናው ግርዶሽ ምሽት 5:14 ላይ እንደሚታይ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጄኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ግርዶሹ ያለምንም መሳርያ በዓይን ብቻ የሚታይ ሲሆን ቴሌስኮፕ እና ባይኑክላር ተጠቅሞም ማየት እንደሚቻልም  ከኢንስቲትዩቱ ጠቅሷል።

በመጀመሪያ ጨረቃ በመሬት ድብዝዝ  ስለምትል በባዶ ዓይን እንደማይታይ የተነገረ ሲሆን ፤ በመቀጠል ጸሊም ጥላ ወይም አምብራ በሚባለው ከፊል ግርዶሽ ውስጥ ትገባለች ተብሏል። ኢንስቲትዩቱ በዋናው የግርዶሹ ቅፅበት ወቅትም የጨረቃ 12 በመቶ አካሏ ብቻ የተጋረደ ይሆናል ብሏል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.2K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-25 06:51:57
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአሜሪካ ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ሽልማት ተሰጣቸዉ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማትን መቀበላቸውን የብልጽግና ፓርቲ አሳዉቋል።

ከንቲባዋ ለሕዝብ ተጠቃሚነት እና ለሰላም ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅዖ ፣ ያሳዩት በሳል እና ምሳሌያዊ አመራር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ መሪዎች  ምሳሌ የሚሆንና መነሳሳት የሚፈጥር በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ይህንን Doctorate of Philosophy  እንዳበረከተላቸው ተነግሯል።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ለሌሎች ሃገራት መሪዎች አርአያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማት እንደተበረከተላቸው የግዛቱ ሴናተር ጋይል ዴቨንፓርት በመድረኩ ላይ ተናግረዋል ተብሏል::

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.7K viewsedited  03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 15:25:18
በቻይና አረጋውያን ባልና ሚስት ከመንግሥት ለመንገድ ግንባታ ከመኖሪያ ቤታቸው ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው።

የሚከፈለው የካሳ ክፍያ በቂ እንዳልሆነ በመግለጽ ለመንቀሳቀስ ፈቃደኛ አልሆኑም። በምላሹ መንግሥት መንገዱን በዙሪያቸው ሠራ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.8K viewsedited  12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-19 12:10:10
አንጋፋው የእሁድን በebs አቅራቢ አስፋው መሸሻ ላለፉት ሁለት ሳምንታት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል ሆስፒታል(ገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል) ህክምናውን እየተከታተለ መቆየቱን ይታወቃል።

ይሁንና እስትሮኩ በአንድ በኩል ያለው የሰውነት ክፍሉ ላይ ያደረሰው ጉዳት ምንም መሻሻል ባለማሳየቱ ትላንት ማክሰኞ ምሽት ጥቅምት 6 ለተሻለ ህክምና ወደ አሜሪካ መጓዙን ሰምተናል።(ዘሐበሻ)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.1K viewsedited  09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-14 23:34:32
በኬንያ ምንም አይነት የህግ ትምህርተ ሳይወስድ በሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ጠበቃ ሆኖ የሰራ ግለሰብ ተያዘ

ግለሰቡ 26 ክሶችን ጠበቃ ሆኖ ሁሉንም ረቷል።

ነገር ግን በህግ የዲፕሎማም ሆነ የዲግሪ ት/ ት የሌለው መሆኑም ተረጋግጣል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑን ዘግበዋል።

27ኛው ክስ የራሱ መሆኑ ነው እንግዲ!

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.1K viewsedited  20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-14 07:47:36
" የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል "

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጨርሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በርካቶችም ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ጨርሰው ወደ ተንቤን እና አካባቢው ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን አስፋሮ የነበረ ኣውቶብስ በሀውዜን ወረዳ " ደብረ ሰላም " የሚባል አካባቢ ተገልብጦ የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው ​​ከሞቱት 6 ተማሪዎች በተጨማሪ 53 ተማሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀውዜን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አሳውቋል።

የሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የመጋብ ጤና ጣቢያ የህክምና እና የአምቡላንስ ባለሙያዎች ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ጉዳት የደረሰባቸው 29 ተማሪዎች በሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና መጋብ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ሲሆኑ ፤ 24ቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.4K viewsedited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 08:43:23
የ12ኛ ክፍል ውጤቴ ትዝ አለኝ!

የዛሬ ስንት አመት እኔም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ነበርኩኝ፡፡ አሁን ብዙዎቻችሁ እንደሆነባችሁ የያን ጊዜ ውጤቴ በፍጹም ያልጠበኩት ነበር፡፡ ያገኘሁት ውጤቴ ይቅርባችሁ፣ አይገለጽ 

በዚያ ጊዜ መጥቶብኝ የነበረውን ስሜት እስካሁን አስታውሰዋለሁ፡፡

•  ከትምህርት አንጻር አቅጄው የነበረኝ ህልሜ ሁሉ ጨልሞብኝ ነበር፡፡

•  ለትምህርት ትኩረት የሰጠውም ሆነ ያልሰጠውም ሰው አንድ አይነት እንደሆነና የመማር ትጋት ትርጉም እንደሌለው እንዳስብ ሆኜ ነበር፡፡

•  ከእኔ ብዙ ይጠብቁ የነበሩት የወላጆቼና የቤተሰቦቼ ነገር አስጨንቆኝ ነበር፡፡

•  ሕይወቴን እንዴት እንደምቀጥልና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ግብት ብሎኝ ነበር፡፡

•  ስለውጤቴ የሚጠይቁኝ ሰዎች ሁኔታ አሸማቆኝ ነበር፡፡

•  በአጭሩ ዞሮብኝ ነበር!!!

ሆኖም፣ የያን ጊዜው ውጤቴ የዛሬውን ሕይወቴን አልወሰነውም፡፡ የዛሬውን ሕይወቴን የወሰነው ለነበረኝ ውጤት የሰጠሁት ምላሽ ነው፡፡

የፈተና ውጤት ላልመጣላችሁ . . .

1.  ሁኔታው ስሜታችሁን መንካቱ ጤናማ ሂደት እንደሆነ አስታውሱ

2.  የእናንተን የወደፊት ሕይወት የሚወስነው ራእያችሁን ማወቃችሁና ያንን መከተላችሁ እንጂ በየጊዜ የምትወድቁትና የምትነሱት ልምምድ እንዳልሆነ እወቁ

3.  ሰዎች ለሚሰነዝሩት ሃሳብ ብዙ ቦታ አትስጡ፡፡ ብዙዎቹ ሰዎች ለራሳቸው እንኳን ያላወቁበት ሰዎች ናቸው፡፡

4.  ለሁኔታው የምትሰጡትን ምላሽና የሚቀጥለው እርጃችሁ ምን ሊሆን እንደሚገባው ተረጋግታችሁ አስቡ፡፡

ወደቃችሁ እንጂ ውዳቂ አይደላችሁም!

ውጤት ባይመጣም እናንተ ግን ወደ ወደፊት ራእያችሁና መልካም ፍጻሜያችሁ ትቀጥላላችሁ!

Dr Eyob mamo

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.0K viewsedited  05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 12:19:43 ውጤታችሁን በቀላሉ በ  20 sec ለማየት

ይሄንን ሊንክ ከታች በተዘረዘረው step መሰረት edit አድርጋችሁ መጠቀም ነው

https://Verify.eaes.et/temporary/FNLNMN=ID

FN ማለት ከራሳችሁ ስም ላይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ፊደል
LNከአያታችሁ ስም ላይ የመጀመሪያው ሁለት ፊደል
MN ከአባታችሁ ስም ላይ የመጀመሪያ ሁለት ፊደል አድርጋችሁ iD ላይ reg number መፃፍ

ማሳሰቢያ

1 ቅደም ተከተል እንዳትሳሳቱ ከስማችሁ ከአያታችሁ ስም ከዛ ከአባታችሁ ሁለት ፊደል
2 ሁሉ በcapital መሆኑን እንዳትረሱ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.8K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ