Get Mystery Box with random crypto!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአሜሪካ ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ሽልማት ተሰጣቸዉ ከንቲባ አዳነ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአሜሪካ ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ሽልማት ተሰጣቸዉ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማትን መቀበላቸውን የብልጽግና ፓርቲ አሳዉቋል።

ከንቲባዋ ለሕዝብ ተጠቃሚነት እና ለሰላም ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅዖ ፣ ያሳዩት በሳል እና ምሳሌያዊ አመራር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ መሪዎች  ምሳሌ የሚሆንና መነሳሳት የሚፈጥር በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ይህንን Doctorate of Philosophy  እንዳበረከተላቸው ተነግሯል።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ለሌሎች ሃገራት መሪዎች አርአያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማት እንደተበረከተላቸው የግዛቱ ሴናተር ጋይል ዴቨንፓርት በመድረኩ ላይ ተናግረዋል ተብሏል::

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS