Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ምሽት 4 :35 ላይ ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ እንደሚታይ ተነገረ ዛሬ ምሽቱን ጨረቃ የተወሰነ ከ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ዛሬ ምሽት 4 :35 ላይ ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ እንደሚታይ ተነገረ

ዛሬ ምሽቱን ጨረቃ የተወሰነ ከፊል አካሏ የመሬት ጥላ ሲያርፍበት እንደሚሸፈንና  ይህም ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ እንዲከሰት እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጄኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ግርዶሹ ዛሬ ምሽት ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም በሁሉም የአፍሪካ ክፍል ይታያል የተባለ ሲሆን ከፊል ግርዶሹ ከምሽቱ 4:35 ጀምሮ ምሽት 5:53 ላይ እንደሚያበቃ የተገለጸ ሲሆን፤ 6 በመቶ የሆነው ዋናው ግርዶሽ ምሽት 5:14 ላይ እንደሚታይ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጄኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ግርዶሹ ያለምንም መሳርያ በዓይን ብቻ የሚታይ ሲሆን ቴሌስኮፕ እና ባይኑክላር ተጠቅሞም ማየት እንደሚቻልም  ከኢንስቲትዩቱ ጠቅሷል።

በመጀመሪያ ጨረቃ በመሬት ድብዝዝ  ስለምትል በባዶ ዓይን እንደማይታይ የተነገረ ሲሆን ፤ በመቀጠል ጸሊም ጥላ ወይም አምብራ በሚባለው ከፊል ግርዶሽ ውስጥ ትገባለች ተብሏል። ኢንስቲትዩቱ በዋናው የግርዶሹ ቅፅበት ወቅትም የጨረቃ 12 በመቶ አካሏ ብቻ የተጋረደ ይሆናል ብሏል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS