Get Mystery Box with random crypto!

በአሜሪካ ቤቷን ሰብሮ ሶፋ ላይ በድፍረት የተኛውን  ሰው  ያገባችው  ሴት አነጋጋሪ ሆናለች ነገ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በአሜሪካ ቤቷን ሰብሮ ሶፋ ላይ በድፍረት የተኛውን  ሰው  ያገባችው  ሴት አነጋጋሪ ሆናለች

ነገሩ እንዲህ ነው;

ካትሪን የተባለችው የኒው ዮርክ ነዋሪ ከስድስት አመት በፊት  አንድ ቀን ጠዋት ስትነሳ ቤቷ ሳሎን  አንዱ  መስኮት  ተሰብሮ  ተመለከተች ።  ሳሎን  ትልቁ ሶፋ ላይ የተኛ  የሚያንኮራፋ የወንድ  ልጅ ድምፅ ሰማች። ደነገጠች።

ቤቷ ከእህቷ በቀር  መጥቶ የሚተኛ እንደሌለ ታውቃለች።

እህቷ ጋር ስትደውል እንዳልመጣች እና ቤተሰብ ጋር እንዳደረች ነገረቻት ።

ፖሊስ ጠራች ። ሰውዬው ከተኛበት ተቀሰቀሰ ። በሰጠውም ምላሽ ማታ ክለብ እንደነበረና  ጠጥቶ ስለነበረ   እንዴት እንዲህ እንዳደረገ እንደማያውቅ ተናገረ።

ካትሪን ቤቷን ያለውን ዕቃ ሁሉ አበጥራ ፈተሸች። ምንም የተወሰደ ነገር የለም።


ሚካኤል ጆንስተን የተባለው ሰው ወደ ጣቢያ ተወሰደ ። ካትሪን ሰወዬው እንቅልፍ ጥሎት ይሆናል ቤቴ መጥቶ የተኛው በማለት መክሰሱን ተወችው።

ሚካኤል ጆንስተን  ከፖሊስ ጣቢያ  ከተለቀቀ በኃላ   በአንዱ ቀን ያደረገውን ነገር  በቀና ተመልክታ የሰራውን ወንጀል  ይቅርታ በማለቷ  ልብ የሚነካ የምስጋና ደብዳቤ ከአበባ ጋር ለካትሪን ላከላት።

ካትሪን  ከሰውዬው ጋር  መቀራረብ ጀመረች  ። ቅርርባቸው አድጎ ሰሞኑ እንደተጋቡ  ዴይሊ ኒዮርክ ዘግቧል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS