Get Mystery Box with random crypto!

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ የአቅም ማሻሻያ (Rem | 🇪🇹 ኢትዮ Students

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በኹሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግሥት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም መሠረት፦
የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 255 ያመጡ

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 -234 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600- 218 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 200 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 224 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 192 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ  ተማሪዎች  ከ600 - 180  ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180  ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።
___

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS