Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-06-07 07:57:02
በቻይና የ13 ዓመቷ ታዳጊ በሞባይል ጌም ጨዋታ ከእናቷን ባንክ አካውንት 3.4 ሚሊዮን ብር(63 ሺ ዶላር) ማጥፋቷ ተሰማ

በቻይና ሄናን ግዛት የምትኖረው የ13 ዓመቷ ታዳጊ በሞባይል ጌም ሱስ ውስጥ ከገባች በኃላ 3.4 ሚሊዮን ብር ወይም (63,000 ዶላር) ለሞባይል ጌም እንዳወጣች ወላጆቿ ማወቃቸው አስደንግጧቸዋል።ለዓመታት ገንዘብ ሲቆጥቡበት የነበረውን የቁጠባ ሂሳብ ሲፈትሹ በአንድ ጀምበር ተሟጦ ተመልክተዋል።

የ13 ዓመቷ ልጅ የእናቷን የዴቢት ካርድ ተጠቅማ የቪዲዮ ጌም ሱሷን ለማቀጣጠል ስትጠቀምበት ቆይታለች።ልጅቷ የቁጠባ ሂሳቡን በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ማሟጠጥ ችላለች። ነገር ግን ከባንክ የሚላከውን አጭር የፅሁፍ መልዕክት ከእናቷ ስልክ ላይ ስታጠፋ ቆይታለች።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
7.2K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 14:24:56
በታላቁ አንዋር መስጊድ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉና በርካቶች መጎዳታቸው ተሰማ

በታላቁ አንዋር መስጅድ በዛሬው እለት የተካሔደ ተቃውሞ ባይኖርሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይል ግን ወደ ህዝቡ ቀጥታ መሳርያ እየተኮሰ እንደሆነ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለሀሩን ሚዲያ ገልጸዋል።

እስካሁን ቁጥራቸው በቅጡ ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎችም መጎዳታቸውን አብረው ገልጸውልናል። ጥቃቱ ወደ ሴቶች መስጅድም የዘለቀ ሲሆን ሴት ምዕመናኖች ላይም የጸጥታ አካሉ የጥይት እሩምታ መክፈቱን ለማወቅ ችለናል። ዝርዝሩን እየተከታተልን ሲሆን መረጃዎችን ወደናንተ የምናድርስ ይሆናል።

Via ሀሩን ሚዲያ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.3K views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 20:15:10 በአዲስ አበባ ዉስጥ በተመረጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በበዓላት ቀናት መስራት ግዴታ ሊሆን ነው ተብሏል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የአገልግሎት መስጫ ጊዜን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ የተለየ ትኩረት ይፈልጋል የሚል እምነት አለን ብለዋል፡፡

በመዲናዋ የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም መፈጠር አለበት ነዉ ያሉት፡፡

በመዲናዋ የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን አገልግሎት በአሰራር ተዘርግቶ መተግበር አለበት ብለዋል፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደር ከመደበኛዉ 8 ሰዓት ተጨማሪ መስራት ያለባቸዉ መስሪያ ቤቶች የትኞቹ ናቸዉ? የሚለዉ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ባለዉ የትራንስፖርት መጨናነቅ እና በተለያዩ ጉዳዮች ሰራተኛዉ ቢሮ ገብቶ የሚሰራበት ሰዓት ዉስን በመሆኑ ሰዉ ማግኘት ያለበትን ተገቢዉን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
10.7K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 15:45:27 Abbrevations for chatting online:

2 = to
2 mrw = tomorrow
4 =  for
AFK = away from keyboard
AKA = also known as
ASAP =  as soon as possible
A/S/L =  age/sex/location
AYT = Are you there?
B2W = back to work
B4 = before
BBL =  Be back later
BBS = Be back soon
BF = boyfriend
BFF = best friend(s) forever
BRB = Be right back
BTW = by the way
CMB  = Call me back
CMIIW = Correct me if I’m wrong
CU  = See you
CU L8R = See you later
CUZ/COS = because
CWYL = Chat with you later
DC = disconnected
DIY = Do it yourself
DM = Direct Message
F2F = face-to-face
FAQ = frequently asked questions
FB = Facebook
FYI = for your information
FYEO = for your eyes only
GB = goodbye
GF = girlfriend
GG = Gotta go
GL = good luck
GR8 = great!
HBD = Happy Birthday
hhhhhh = very funny
How r u = How are you?
IC = I see
IDK = I don’t know
IMHO = in my humble opinion
IK = I know
IM = Instant Message
IOW = in other words
J/K = just kidding
K = OK
L8R = later (goodbye)
LOL = laugh out loud
M/F = male or female?
mins = minutes
MSG = message
nv = nevermind
OIC = Oh, I see
OTW = on the way
P2P = person-to-person
PLZ = please
PM = Private Message
RUOK = Are you okay?
Sup or Zup = What’s up?
SYL = See you later
TGIF Thank = goodness it’s Friday
THX or thnx = thanks
TYT = Take your time
u = you
U2 = you too
ur = your / you’re

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.6K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 11:24:46
በትራፊክ አደጋ 15 የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ህይወታቸው አለፈ

15 የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን ህይወት ማለፉን ገልፀዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
16.4K viewsedited  08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 14:03:30
12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን አሳውቋል።

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
15.7K viewsedited  11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 16:45:54
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ አሟልተው የላኩ 158 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

እስካሁን የተሟላ ዝርዝር ከላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ፣ ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ፣ አድማስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል።

በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላኩ ተማሪዎችን መረጃ እያጣራ መሆኑን የገለጸው ባለሥልጣኑ፤ የተማሪዎችን መረጃ አጣርቶ እንደጨረሰ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን ዝርዝር እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

(የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን የተሟላ መረጃ የላኩ 158 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.9K views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:07:48
#የሐዘን_መግለጫ!

●●●●●

የአንደኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪያችን የነበረው ተማሪ አበባው  ስንሻው መጸዳጃ ቤት ውስጥ ገብቶ  የመጸዳጃ ቤቱን  በር በመቆለፍ በራሱ ቀበቶ ራሱን አጥፍቶ በመገኘቱ ዩኒቨርሲቲያችን የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል። ተማሪው እዚህ አሳዛኝ ውሳኔ  ላይ እንዲደርስ ያበቁትን ጉዳዩች ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልግ ቢሆንም ፈተና ከበደኝ በሚል ሲጨናነቅ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ስለሆነም ለቤተሰቦቹ ፣ ለጓደኞቹና ለዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን!

              ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.1K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 16:46:17
ተያዘች

2 ህፃናት በመግደል የተጠረጠረችው ነጋሴ ከበደ ጫካ ውስጥ ተያዘች

የ2 ህጻናት ልጆችን በቢላዋ አርዳ በማቃጠል ገላ የተሰወረችው ተጠርጣሪ ነጋሴ ቡራዬ ሳንሱሲ ጫካ ውሰጥ አሁን ተይዛለች።

ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር ሲያዉላት ጫጃ ዉስጥ ራሷን ለማጥፋት ገመድ እና በረኪና ይዛ እንደነበር ዋና ሳጅን ጫላ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.9K views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 09:36:18
በቡራዩ ሁለት ህጻናት በአሳዳጊያቸዉ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

በሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክ/ከተማ ከታ በተሰኘዉ አካባቢ እድሜያቸዉ የ 12 እና 4 አመት የሆኑ ወንድምና እህት በአሳዳጊያቸዉ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

የ12 አመት ታዳጊ የሆነዉ ናኦል ጌቱ እና የ 4 አመቷ ህጻን የሆነችዉ ናኑ ጌቱ ከትናንት በስቲያ ሌሊት የቤት ሰራተኛ ሆና ወደ ቤታቸዉ በገባችና በኋላም ከሟቾቹ ህጻናት አባት ጋር የፍቅር ግንኙነት አላት በተባለችዉ "ነጋሴ ከበደ" ግድያ ተፈጽሞባቸዋል። ግለሰቧ ህጻናቱን በማረድ ከገደለች በኋላ አስክሬናቸውን በእሳት ማቃጠሏም ነዉ የተሰማዉ።

በሸገር ከተማ የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ለኪሳ በተለይ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት ፤ ግለሰቧ ራስዋን "ትግስት" ብላ የምትጠራ ሲሆን ድርጊቱን ከፈጸመች በኋላ ከአካባቢዉ መሰወሯን ገልጸዋል።

"ነጋሴ ከበደ" አልያም ራሷን "ትግስት" የምትለዉ ግለሰብ ፤ ከሟች ህጻናቶቹ አባት ጋር ግንኙነት እንደነበራቸዉና ከሶስት ወራት በፊት ተጋጭተዉ ከቤት መዉጣቷን ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ተናግረዋል። በኋላም በእርሷ ቤተሰቦች አሸማጋይነት ሁለቱ ጥንዶች እርቅ አድርገዉ ወደ ቤት መመለሷን ይገልፃሉ።

ሆኖም አባት በከተማዉ ባለ የቄራዎች ድርጅት ሰራተኛ እንደመሆኑ እንደተለመደዉ ከትናንት በስቲያም በሌሊት ወደ ስራ ያቀናል። በዚህ ወቅትም ግለሰቧ ቤቱ መቃጠሉን ለአባት በስልክ ታሳዉቃለች። በኋላም አባት በቦታዉ ሲደርስ እና የህጻናቱ አስክሬን ሲገኝ ህጻናቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ይረጋገጣል።

ግለሰቧም ከአካባቢው ራሷን መሰወሯን እና ፖሊስም በፍለጋ ላይ መሆኑን በሸገር ከተማ የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ለኪሳ ጨምረዉ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

@ETHIOSTUDENTS
8.7K views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ