Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-06-28 16:29:27
አንጎላችን የአመለካከት ህጎችን ስለሚያውቅ የሩቅ ሰማያዊ መስመር ከፊት ለፊት ካለው አረንጓዴ መስመር የበለጠ ረጅም ነው ብለን እናስባለን ። እንደ እውነቱ ከሆነ ተመሳሳይ ርዝመት አላቸው።

ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
9.8K viewsedited  13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 07:30:00
ውፍረቴ ለባንክ ብድር ይጠቅመኛል ብለው አስበው ያውቃሉ?


በኡጋንዳ ወፈር ያሉ ሰዎች ሀብታም ናቸው ተብለው ስለሚታመኑ ከባንክ ብድር ለማግኘት ብዙም አይቸገሩም ሲል የአሜሪካ ኢኮኖሚክ ሪቪው በጥናት ደርሼበታለው ብሏል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
10.2K viewsedited  04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 06:31:32
ለእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የዒድ ዓል አድሃ ( አረፋ) በአል ይሁንላቹ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
8.5K viewsedited  03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 11:31:50
የኳሶቹ  ቀለም የተለያየ ይመስለል ።ቀረብ ብለው ሲያዯቸው ግን ሀሉም ቡኒ ናቸው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
9.4K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 10:42:14 በአዲስ አበባ ከተማ ትቦ ዉስጥ ተጥሏል ተብሎ በስካቫተር ሲፈለግ የነበረው የጨቅላ ህጻን ድምጽ የአምስት ቡችሎች ሆኖ ተገኘ

በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ከቀኑ 9:30 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 መሳለሚያ ሸዋ ጸጋ ገበያ ማዕከል ፊት ለፊት ነው። በስፍራው የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦ ዉስጥ  የጨቅላ ህጻን ድምጽ መስማታቸዉን ተከትሎ የአካባቢዉ ህብረተሰብ ለእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መደወላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቃል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና መረጃዉ የደረሰዉ ፖሊስ በስፍራው ላይ መድረሱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከትቦዉ ዉስጥ እየሰሙ ያለውን  ድምጽ ተከትለዉ በእስካቫተር ማሽን ታግዘዉ እየጣለ የነበረዉ ከባድ ዝናብ ህጻኑን በጎርፍ እንዳይወሰድ በከፍተኛ ፍጥነትና ጥንቃቄ ድምጽ የሚሰማበትን ጆንያ ከጉድጓዱ ወስጥ አዉጥተዉታል።

በርካታ ሰዎች  የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ፖሊሶች ህጻን በጆንያ ተጠቅልሎ ተጥሎ ነዉ የሚል ጥርጣሬ ቢኖርም ከትቦ ዉስጥ የተገኘዉ ህጻን ልጅ ሳይሆን በጆንያ የተጠቀለሉ አምስት ጨቅላ ቡችሎች ሆነዉ መገኘታቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ወደ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያደረገው ወጣት በየግዜው ጨቅላ ሕፃናት በትቦ እና በመፀዳጃ ቤት ተጥለው መገኘታቸው መረጃ ስለሚሰማ ከጉድጓድ ውጥ የሰማው ድምፅ የተጣለ ሕፃን ነው የሚል እርግጠኝነት እንደነበረው አስታወቋል።

በትግስት ላቀው

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
8.9K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 13:37:32 #ይደመጥ

- የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ጉዳይ እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስጋት

- የተማሪዎች ምረቃ እና የመውጫ ፈተና መያያዝ

- የሬሜዲያ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ

- የትምህርት ጥራት እና ፈተና

እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮች የተዳሰሰበት " ፋና ቴሌቪዥን " ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ከላይ በድምፅ ፋይል ተያይዟል።

ፋይሉ 13 MB ነው።

Credit - #FBC

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
9.8K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 09:51:47
#top_10_Strongest_currencies_in_the_world

በ2023 እ.ኤ.አ የአለማችን ጠንካራ መገበያያ ገንዘብ ያላቸው 10 ሀገራት በቅድመ ተከተል እነሆ ፦

1. Kuwaiti dinar (KWD)
2. Bahraini dinar (BHD)
3. Omani rial (OMR)
4. Jordanian dinar (JOD)
5. British pound (GBP)
6. Cayman Islands dollar (KYD)
7. Gibraltar pound (GIP)
8. Swiss Franc (CHF)
9. Euro (EUR)
10. US dollar (USD)

via - Forbes

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
10.9K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 19:23:42
የመውጫ ፈተና !

ከ168 ሺ በላይ የ2015 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች በቀጣይ ወር የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ።

የመውጫ ፈተናው ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በኦንላይን በ208 የትምህርት መስኮች ይሰጣል።

መንግሥት ከዚህ ቀደም ፈተናው ለ240 ሺህ በላይ ዕጩ ተመራቂዎች ይሰጣል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ ፈተናውን ለመውሰድ 168,345 ተማሪዎች ብቻ #መስፈርት ማሟላታቸው ተገልጿል።

ከ44 የመንግሥት እና ከ161 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን በ82 የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ይወስዳሉ።

ከሐምሌ 09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ውጤት ይገለጻል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን የተመለከተ መረጃ ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኝ ተማሪዎቻቸውን የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣለትን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኝ ተማሪዎች የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል እንዲወስዱ ለተቋማቱ ጥሪ አድርጓል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.1K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 19:39:02
''ተስፋዬ'' በኢትዮጵያ በብዛት ጥቅም ላይ የዋለ ስም ነው

የተለያዩ  መስፈርቶችን በመጠቀም ደረጃዎች በማውጣት የሚታወቀው The World Ranking በኢትዮጵያ በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው የአያት ስም ተስፋዬ የሚል ነው ይላል።

በአሜሪካ በአውስትራሊያ በእንግሊዝ እና በካናዳ አያቶች በአብዛኛው ስሚዝ የሚባል ስም አላቸው።

ፖርቹጋል- ሲልቫ፥ ብራዚል -ዴ ሲልቫ፥ ጀርመን -ሙለር፤ ኢራቅ- መሃመድ፥ ሳኡዲ አረቢያ እና አረብ ኢምሬቶች ደግሞ አሊ የሚሉ መጠሪያ ስሞች በተለይ በአያቶቻቸው ዘንድ የተለመዱ ናቸው ይላል መረጃው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
11.7K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 20:51:55
ባለፈው ሳምንት ሊቀበሩ ሲሉ ሬሳ ሳጥን አንኳክተው የተነሱት ኢኳዶራዊ ሴት ዛሬ መሞታቸው ተነገረ

የ76 ዓመቷ ቤላ ሞንቶያ ሞተዋል ተብለው ለአምስት ሰአት ሬሳ ሳጥን መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን ለአንድ ሳምንት ፅኑ ህመማን ክፍል ውስጥ ከቆዩ በኋላ ዛሬ መሞታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
11.5K viewsedited  17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ