Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-09-15 21:50:40
የፋይናንስ ማጭበርበርን ለመከላከል ቴሌብር በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ ተደረገ።

የዲጂታል ክፍያና ሥርዓት እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት የማጭበርበሪያ ስልቱም ሆነ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል። ይህን ተከትሎ የፋይናንስ ተቋማት በተለይ በዲጂታል መተግበሪያዎቻቸውን ያዘምናሉ።

በኢትዮጵያ 36 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉት ያስታወቀው ቴሌብር በደንበኞቹ ላይ የሚደርሰውን መጭበርበር ይቀርፋል ያለውን ማዘመኛ ይፋ አድርጓል። 

ማዘመኛው፥ ስልክ በመደወል፤ የፒን ቁጥርን በማታለል በመቀበልና በሌላ ስልክ በመጠቀም አካውንቱ ላይ የሚገኝ ገንዘብን በማዘዋወር የሚፈጸምን ማጭበርበር ለመግታት እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

- ደንበኛው የራሱ ስልክ ቁጥር ባለበት የሞባይል ቀፎ ካልሆነ በስተቀር በሌላ አገልግሎት ቁጥር (ሲም ካርድ) እንዳይሰራ፣

- የራሱን ስልክ የሞባይል ዳታን በመጠቀም ካልሆነ በስተቀር በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ የተደረገ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.2K viewsedited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-07 12:26:03
ሁለት ቤተሰቦችን ያጨቃጨቀዉ ከሞት ተነሳ የተባለዉ ታዳጊ ጉዳይ እልባት ማግኘቱ ፖሊስ አስታወቀ

በስልጤ ሁልባራግ ወረዳ ቢለዋንጃ ቀበሌ  ከአራት አመት በፊት ሞቶ ተቀብሯል የተባለዉ ታዳጊ ባቂ ሲከማ መሀመድን  ከመንገድ ላይ ያገኙት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም  ለቤተሰቡ አስረክበዋል።

የታዳጊዉ ቤተሰቦችም  ሟች ልጃቸዉ ባቂ ስለመሆኑ አንዳችም የሚያጠራጥር ነገር እንደሌለዉ አረጋግጠዉ ተደስተው ፈጣሪ ከሞተ በኋላ አስነስቶ ህያዉ አድርጎታል ሲሉ ታዳጊዉን ተቀብለዉ እንደወትሮዉ መንከባከብ መጀመራቸዉ ተነግሮ ነበር።

በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ታዳጊ ጋር ሁለንተናዊ መመሳሰል ያለዉ  አብዲ ሄራቶ አቦዬ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ  ቤተሰቦች ከሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ አከባቢ ልጃችን ነው ይሰጠን ሲሉ የመጡ ሲሆን በሁለቱ ቤተሰቦች መሀከል የይገባኛል ጥያቄ  መነሳቱም ቀደም ሲል ተገልጿል።

አሁን የሁለቱ ቤተሰቦች የይገባኛል ክርክር መቋጫ ማግኘቱ የሁልባረግ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።ፖሊስ ፣ዐቃቤህግና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ባደረጉት ማጣራት አብዲ ሄራቶ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ ቤተሰቦች መሆኑ የሚያሳይ በእጅና በእግሩ የተነገሩ  ልዩ ምልክቶችን መኖራቸዉ በማረጋገጥ ታዳጊዉ ጠፍቶብናል ለሚሉ ቤተሰቦች ተላልፎ መሰጠቱ የሁልባረግ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።

ስለዚህ ከአራት አመት በፊት ሞቶ የተቀበረዉ ታዳጊ ከሞት አለመነሳቱ ህብረተሰቡ እንዲያዉቀዉ ሲል ፖሊስ አሳስቧል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-27 10:18:17
ከኢየሱስ ጋር ካልሆነ ከሰይጣን ጋር ቻት ማድረጊያ አፕ ተሰራ

አዲስ AI chatbot መተግበሪያ "ቴክስት ከኢየሱስ ጋር" በሚል ተጠቃሚዎች እንደ ኢየሱስ በተጨማሪም ሌሎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ነብያትና ታሪካቸው ከተጠቀሱ ሰዎች ጋር ስማቸውን እየተጠራሩ ውይይት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል። ሆኖም ተጠቃሚዎች በሌላ በኩል የ AI chatbot መተግበሪያን ሲጠቀሙ ከሰይጣን ጋር መወያየት የሚያስችል መሆኑ ውዝግብ አስነስቷል።

አፕሊኬሽኑ የተዘጋጀው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በመጠቀም ነው። የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ብቅ ማለት የሁሉንም ሰው ህይወት እያሻሻለ ሲሆን በቴክኖሎጂ ኢንደስትሪው ውስጥ ብቻ ሳይሆን AI የመምህር፣ አጋር እና አልፎ ተርፎም የስነ ከዋክብትን ሚና በመጫወት የሰዎች ህይወት አካል እየሆነ እንደሚገኝ ሎስ አንጀለስ ውስጥ መሰረቱን ያደረገው ካት ሉፍ የሶፍትዌር ኩባንያ አስታውቋል።


አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሰዎችን ከመለኮታዊው ዓለም ጋር እንዲያገናኝ አስችሏል ሲል ኩባንያው ገልጿል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.0K viewsedited  07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-11 11:26:17
እስከ 3 አመቷ መናገር ያልቻለችው ህፃን በእንግሊዘኛ ቋንቋ አፏን ፈታች

ነገሩ የሆነው በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ውስጥ ነው፤ ህጻን ሮሆቦት ሐፌ ትባላለች፤ እስከ 3 አመቷ መናገር አትችልም ነበር፤ ከ3 አመት በኋላ ቀስበቀስ የተለያዩ ፍላጎቷን በእንግሊዘኛ መግለፅ ጀመረች።

አቶ ሐፌ ቤተሰብ የመንግስት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ህፃናት መካከል የእሳቸው ልጅ እንግሊዘኛ መናገር መጀመሯ እንዳስገረማቸው ተናግሯል።

ሮሆቦት በሰፈርም እንግሊዘኛ ብቻ ስለምትናገር ቤተሰብ እንግሊዘኛ ለማናገር መገደዳቸውን ይናገራሉ። እንግሊዘኛ ብቻ የሚያስተምር ትምህርት ቤት በአካባቢው አለመኖሩ የትምህርቷ ጉዳይ አሳስቦኛል ሲሉ አባት ተናግሯል።

FastMereja

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.0K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-01 22:41:45
ክርስቶስ ወደ ምድር በቶሎ ለፍርድ እንዲመጣ በሚል ሁለት ልጆቿን የገደለችው እናት ተፈረደባት።

በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት እናት በአፖካሊፕቲክ ሃይማኖታዊ እምነቷ መሰረት ሁለት ልጆቿን በመግደል እና የባሏን የቀድሞ ሚስት ለመግደል በማሴር የእድሜ ልክ እስራት ተፈርደባት።

ሎሪ ቫሎው የተባለችዉ ይህችዉ ሴት በግንቦት ወር የ16 ዓመቷን ሴት ልጇን ታይሊ ራያን  እና የሰባት ዓመት በማደጎ የወሰደችዉን ወንድ ልጇን ኢያሱ "ጄጄ" ቫሎውን በመግደል ጥፋተኛ ተብላለች፡፡

የእናታችን ኃጢአት (Sins of Our Mother) በሚል የዚህችዉ ሴት የህይወት ታሪክ በኔትፍሊክስ እውነተኛ የወንጀል ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምጽዓት እንዲሆን ልጆቿን መግደሏ ከአምላክ የተሰጠ ራዕይ መሆኑን ትናገራለች፡፡

ዳኛ ስቲቨን ደብሊው ቦይስ በቫሎው የወንጀል ድርጊት ላይ ባሳለፉት የጥፋተኛነት ዉሳኔ በሶስት ተከታታይ የእድሜ ልክ እስራት በይነዋል፡፡

በወላጅ የተፈጸመውን የልጅ ግድያ “በእርግጥ መገመት ከምችለው በላይ አስደንጋጭ ነገር” ሲሉ ዳኛዉ ገልጸዋል።ቫሎው ልጆቿን ከገደለች በኋላ እንደጠፉ ብታሳወቅም  በፖሊስ አስክሬናቸው በፖሊስ መገኘቱን ያስነበበው ዳጉ ጆርናል ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.8K viewsedited  19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-30 08:20:50
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ወደየተመደቡበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግባት ጀምረዋል

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እስከ ነገ ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ። ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም አጠቃላይ ገለጻ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 25 እስከ 28/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.1K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-29 10:17:42
ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተገበር አስገዳጅ መመሪያ ተዘጋጀ

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው ቢያንስ 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት መስኮቻቸው እንዲታጠፉ የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ገልጿል።

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች ለባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 17 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ ማለፋቸው ለመመሪያ መዘጋጀት መነሻ ነው ተብሏል።

Via - FBC

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.3K views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-28 11:38:58
በአዲስ አበባ የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ጉዳዩን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በዘንድሮዉ የ 2015 የትመህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናን አጠቃላይ 73 ሺህ 385 ተማሪዎች መፈተናቸውን አንስተዋል፡፡

ከነዚህ ውስጥም 70 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከደቂቃዎች በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚለቀቁ ሊንኮች መመልከት እንደሚችሉም አስታውቀዋል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.3K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-26 09:30:36
Telegram አሁን ላይ ያለ vpn እየሰራ አይደለም ከፈተና ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል ከታች ያለውን proxy መጠቀም ትችላላቹ

https://t.me/proxy?server=www.welt.website.&port=443&secret=7gAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAB3ZWIuYmFsZS5pcg%3D%3D

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.4K viewsedited  06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 10:43:27
በቶራጃ ኢንዶኔዥያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለሞቱ ቤተሰቦቻቸው ፍቅር ለመግለፅ በዓመት አንድ ጊዜ የሞቱ ዘመዶቻቸውን ከመቃብር አውጥተው ያዝሏቸዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.7K viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ