Get Mystery Box with random crypto!

ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተገበር አስገዳጅ መመሪያ ተዘጋጀ የግል | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተገበር አስገዳጅ መመሪያ ተዘጋጀ

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው ቢያንስ 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት መስኮቻቸው እንዲታጠፉ የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ገልጿል።

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች ለባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 17 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ ማለፋቸው ለመመሪያ መዘጋጀት መነሻ ነው ተብሏል።

Via - FBC

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS