ሁለት ቤተሰቦችን ያጨቃጨቀዉ ከሞት ተነሳ የተባለዉ ታዳጊ ጉዳይ እልባት ማግኘቱ ፖሊስ አስታወቀ
በስልጤ ሁልባራግ ወረዳ ቢለዋንጃ ቀበሌ ከአራት አመት በፊት ሞቶ ተቀብሯል የተባለዉ ታዳጊ ባቂ ሲከማ መሀመድን ከመንገድ ላይ ያገኙት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ለቤተሰቡ አስረክበዋል።
የታዳጊዉ ቤተሰቦችም ሟች ልጃቸዉ ባቂ ስለመሆኑ አንዳችም የሚያጠራጥር ነገር እንደሌለዉ አረጋግጠዉ ተደስተው ፈጣሪ ከሞተ በኋላ አስነስቶ ህያዉ አድርጎታል ሲሉ ታዳጊዉን ተቀብለዉ እንደወትሮዉ መንከባከብ መጀመራቸዉ ተነግሮ ነበር።
በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ታዳጊ ጋር ሁለንተናዊ መመሳሰል ያለዉ አብዲ ሄራቶ አቦዬ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ ቤተሰቦች ከሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ አከባቢ ልጃችን ነው ይሰጠን ሲሉ የመጡ ሲሆን በሁለቱ ቤተሰቦች መሀከል የይገባኛል ጥያቄ መነሳቱም ቀደም ሲል ተገልጿል።
አሁን የሁለቱ ቤተሰቦች የይገባኛል ክርክር መቋጫ ማግኘቱ የሁልባረግ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።ፖሊስ ፣ዐቃቤህግና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ባደረጉት ማጣራት አብዲ ሄራቶ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ ቤተሰቦች መሆኑ የሚያሳይ በእጅና በእግሩ የተነገሩ ልዩ ምልክቶችን መኖራቸዉ በማረጋገጥ ታዳጊዉ ጠፍቶብናል ለሚሉ ቤተሰቦች ተላልፎ መሰጠቱ የሁልባረግ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።
ስለዚህ ከአራት አመት በፊት ሞቶ የተቀበረዉ ታዳጊ ከሞት አለመነሳቱ ህብረተሰቡ እንዲያዉቀዉ ሲል ፖሊስ አሳስቧል።
@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS